
ነገር ግን የኀጢአት ባሮች የነበራችሁ ቢሆንም፣ ለተሰጣችሁለት ትምህርት በሙሉ ልብ የታዘዛችሁ በመሆናችሁ፣ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ (ሮሜ 6:17)
ክርስቶስን እንደ ግል አዳኛችን አድርገን ስንቀበል፣ እግዚአብሔር አዲስ ልብ ይሰጠናል – ትክክል የሆነውን ማድረግ የሚፈልግ ልብ። ሆኖም ባህሪያችን ከአዲሱ ልባችን ጋር አብሮ ለመሄድ ትንሽ ጊዜ ይወስዳል ያ ደግሞ ብዙ ጊዜ በጣም ተስፋ አስቆራጭ ነው። ከፊሉ ማንነታችን ትክክለኛ ነገር ማድረግ ይፈልጋል፣ ሌላኛው ክፍላችን ደግሞ ይህን ይቃረናል። ያ በገላትያ 5፡17 ላይ ጳውሎስ የተናገረው በሥጋና በመንፈስ መካከል የሚደረግ ጦርነት ነው።
በአዲሱ ልደት፣ እግዚአብሔር በቅድስና እና ታዛዥ ሕይወት ለመኖር በሚያስፈልጉን ነገሮች ሁሉ በውስጣችን ያስታጥቀናል፣ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረታት ሆነናል; አሮጌ ነገሮች ያልፋሉ እናም ሁሉም ነገሮች አዲስ ይሆናሉ (2 ቆሮንቶስ 5፡17ን ተመልከት)። አዲስ መንፈሳዊ ሸክላ ሆነናል ማለት እወዳለሁ ደግሞም መንፈስ ቅዱስን በክርስቶስ አምሳል እንዲቀርፀን በመፍቀድ ህይወታችንን እናሳልፋለን (ሮሜ 8፡ 29ን ተመልከት)። መታዘዝ የሚፈልግ አዲስ ልብ ስላገኘን እግዚአብሔርን ማመስገን አለብን።
በእድገትህ ተደሰት ደግሞም እግዚአብሔር ልብህን ስለሚመለከት ተስፋ አትቁረጥ። ከኋላችን ያለውን እየተውን ወደ ሙሉ መታዘዝ መሄዳችንን ከቀጠልን እግዚአብሔር ደስ ይሰኛል። ከእግዚአብሔር ጋር መራመድን እየተማርን ነው፤ መራመድ ደግሞ በጣም ቀርፋፋው የጉዞ ዘዴ ነው። መሆን በምትፈልግበት ቦታ ላይ ላትሆን ትችላለህ፣ ነገር ግን እግዚአብሔርን አመስግን፤ ታዛዥ ልብ አለህ።
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ዛሬ በውድቀቶችህ ላይ ሳይሆን በኢየሱስ ላይ አተኩር።