እግዚአብሔር ሐይላችሁ ነዉ

እግዚአብሔር ሐይላችሁ ነዉ

በተረፈ በጌታና ብርቱ በሆነዉ ኀይሉ ጠንክሩ፡፡ – ኤፌ 6:10

ይጣን ካለዉ ዓላማ መካከል እኛ አማኞችን የዛልን የደከምን ማድረግ እንደሆነ ልብ ልንል ይገባል፡፡ ደንኤል 7፥25 ነብዩ ዳንኤል ስለተቀበለዉ ራዕይ ግልጽ ማብራሪያ ይሰጣል ደግሞም የልዑልንም ቅዱሳን ያስጨንቃል ይለናልም፡፡

ነገር ግን እግዚአብሔር የተበረታታችሁ ትሆኑ ዘንድ ይፈልጋል፡፡ ሮሜ 8፥37 ለክርስቲያኖች ይህንን መልካም ዜና ይሰጣል “በዚህ ሁሉ በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን” “ከአሸናፊዎች እንበልጣለን” ማለት ነዉጥ ከመጀመሩ በፊት ማን እንደሚያሸንፍ እኛ ቀድመን እናዉቃለን ማለት ነዉ፡፡ ያንን እወደዋለሁ፤ እናንተስ?

ከእግዚአብሔር ጋር እንደዚህ ዓይነት ጥብቅ ግንኙነት ይኖረን ዘንድ የልባችንን ዓላማ በጸሎትና በቃሉ መጠገን እንችላለን፡፡ በዚያ በእግዚአብሔር  የተስፋ ቃል ሐይል ውስጥ እንጠነክራለን፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ግንኙነት ሰይጣንን ማሸነፍ የሚችሉ ክርስቲያኖችን ያፈራል፡፡

ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ጥንካሬ ላይ የተደገፈ ሕይወት ኑር፤ ተዋጊዎችን የሚያዝልና ቅዱሳኑን የሚያስፈራ ፍርሃት የሚያመጣ ሙከራ አይኑርህ፡፡ በእርሱና በኀይሉ የበረታህ ሁን፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ አንተ ብቻ ብርቱ ነህ፣ ሳይጣን የዛልኩ ክርስቲያን እንዲያደርገኝ አልፈቅድለትም ነገር ግን ከአንተ ጋር ባለኝ ጥብቅ ግንኙነት ብርቱ ሆኜ እቀጥላለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon