እግዚአብሔር ማንን ይጠቀማል ?

እግዚአብሔር ማንን ይጠቀማል ?

ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ ፤ ብርቱም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤ – 1 ቆሮንቶስ 1፡27

እኔ ለእርሱ እናገርለት እና ቃሉን አስተምርለት ዘንድ እግዚአብሔር እኔን መርጦኛል፡፡ ሰዎች የሚያደምጡኝ እግዚአብሄር እንድናገርለት ስለቀባኝ ነው፡፡ ይህ ለሕይወቴ ያለው የእቅዱ ኣካል ነው፡፡ እግዚአብሔር የወደደውን ሊሰራበት የፈለገውን ሰው ይቀባል፡፡ ይህ ደግሞ አንተንም ይጨምራል፡፡

እግዚብሔር ማንን ነው የሚጠቀመው ? መጽሀፍ ቅዱስ የሚለው የማይመስሉትን ፣ ተራዎችን ፣ እንደ አንተ እና እንደ እኔ ያሉ ልዩ ያልሆንነውን ይጠቀማል፡፡ ወንጌልን መስበክ ስጀምር አንዳድ ጓደኞቼ አልተቀበሉኝም ነበር ፤ ሴት ስለሆንኩ መስበክ ያለብኝ አልመሰላቸውም፡፡ በእርግጥ ማድረግም እንደማልችል ነገረውኝ ነበር፡፡

ነገር ግን እግዚአብሔር አድርጊው ስላለኝ አደረግሁት ፤ እርሱ አድርጊው ካለኝ ማድረግ እንደምችል አመንኩ፡፡ ለአንተም ይሄ እውነት ነው፡፡ በልብህ ግብ እንዲያስቀምጥ ፈቃደኛ ከሆንክ በአንተም ታላቅን ነገር ይሰራል፡፡

እያንዳዱ ተራ ሰው ሀያሉ እግዚአብሔር ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ እርሱ እንደሚጠቀምብህ ማመንና በልብህ ውስጥ ያሰቀመጠውን ግብ እና ራዕይ መያዝ ነው፡፡ ተመርጠሀል!


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ አንተ መርጠኸኛል ፤ ለእኔ ያለህን ፍጻሜ አልጠራጠርም፡፡ በአንተ ውስጥ አላማ ስላላኝ አመሰግንሃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon