. . . ከእንግዲህ ወዲህ አታለቅስም፣ በጩኸትም ድምፅ ይራራልሃል፣ በሰማህም ጊዜ ይመልስልሃል፡፡ ኢሣ 30÷19
የእኛ ኅብረት (ወዳጅነት) እኛን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርግ ብቻ ሳይሆን በእኛ ዙሪያ ያሉትንም ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል፡፡ ሰዎች ወደ እኛ ተቸግረው ወይም ለጉዳይ ሲመጡ እኛ ምናልባት ለችግራቸው እርዳታ ልናደርግም ላናደርግም እንችል ይሆናል፡፡ ምንም እንኳ ሰዎች ከእኛ የሚፈልጉትን ባይኖረንም እንኳ እግዚአብሔር ሁሉን አለው ማድረግም ይችላል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ግንኙነት (ኅብረት) ሲኖረን ለሰዎች እንዲህ ማለት እንችላለን፡፡ አንተ የጠየከኝን እኔ የለኝም፡፡ ነገር ግን አንድ የማውቀው ወዳጅ አለኝ፡፡ እርሱን እጠይቃለሁ በእግዚአብሔር ፊት ለአንተ እማልዳለሁ፡፡
እግዚአብሔር በሰዎች ጉዳይና ሁኔታ ውስጥ ጣልቃ እንደሚገባ እናውቃለን ልጆቻቸው ሃሽሽ ከመጠቀም እንዲያቆሙ ለመርዳት፣ በገንዘብ በረከት ሰብሮ ለመውጣት እንዲችሉ፣ ለታምራዊ ፈውስ፣ ለጋብቻ እርቅና ሠላም ማውረድ ጣልቃ ይገባል፡፡ እግዚአብሔርን በጥልቀት ባወቅን መጠን በታማኝነቱና ሰዎችን ለመርዳት ባለው ችሎታው መታመናችን እርግጠኝነታችን የዛኑ ልክ ይጨምራል፡፡ ስለዚህ ሰዎች ወደ እኛ ሲመጡ እኛም ወደ እርሱ ስለ እነርሱ ስንሄድ፣ እርሱም ወደ ጉዳያቸው ይመጣላቸዋል፡፡ እኛም በእርግጠኝነት እግዚአብሔር በፀጋው እንዲረዳንና ሌሎች የምንወዳቸውን ምንም እንኳ የሚገባቸው ባይሆን እንኳ ይረዳቸዋል ስል እኛ ስል፡፡ እኛ በታላቅ ርህራሄ ያለ ውስጣዊ ፍቅር እንኳ ስንፀልይ እግዚአብሔር ሰምቶ ይመልሳል፡፡ እግዚአብሔር አንተንና በፀሎት ውስጥ የምታሰማውን የአንተን የወዳጅነት ድምፅ መስማት ይወዳል፡፡ ሁልጊዜ ለራስህ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ፍላጎት መፀለይ አለብህ፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- እግዚአብሔር የፀሎት ድምፅህን እንደምወድ አስተውል፡፡