ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሁት መንፈሱም ወደ ተሰበረ በቃልም ወደ ሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ፡፡ ኢሣ 66÷2
ከእግዚአብሔር ስንሰማ፣ በታማኝነትና በትህትና ምላሽ የመስጠት ምርጫ አለን ወይም ደግሞ ልባችንን በማደንደን ችላ ማለት እንችላለን፡፡ ብዙ ሰዎች የሚፈልጉትን ሳያገኙ ሲቀሩ ወይ ደግሞ ለብዙ ሙከራና ፈተና ውስጥ ሲያልፉ በፀፀት ተሞልተው ልባቸው እየደነደነ ይሄዳል፡፡ እስራኤላዊያን በመንገዳቸው እንደዚህ ዓይነት ገጠመኝ በምድረ በዳ ጉዞአቸው ውስጥ በእርግጥ ደርሶባቸው ነበር፡፡ እግዚአብሔር ታላላቅ ነገሮችን ለእነርሱ አቅዶላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን በእርግጥ በእርሱ ያምኑና አያምኑ እንደሆነ ለማወቅ እግዚአብሔር ፈትኖአቸው ነበር፡፡ ትዕዛዙን ይጠብቁና ይከተሉት እንደሆነና እንዳልሆነ ለማወቅ በከባድና በረዥም መንገድ በዓላማው መራቸው፡፡ በቃሉ ውስጥ ልክ እንደ እነርሱ ልባችንን እንዳናደነድን ይነግረናል፡፡ (ዕብ 3÷7-8 ተመልከት) ችግራቸውና መከራቸው እነርሱን መልካም ከማድረግ መራራ አደረጋቸው፡፡ ልባቸውን አደነደነና የእግዚአብሔርን መንገድ ሊማሩ አልፈለጉም፡፡ እግዚአብሔርን ካለመታመናቸው የተነሣ ብዙ ስህተቶችንና ክፉ ልምምድን አዳበሩ፡፡ ከዚህም የተነሣ ለውጥና ዕድገት አላሳዩም፡፡
በተለያዩ ችግሮች ወቅት ልብህ እንዲጠጥር አታድርግ፡፡ ልበ ደንዳና ሰዎች አመፀኞችና ከስህተታቸው ለመታረም ፈቃደኞች አይደሉም፡፡ ከእግዚአብሔር ለመስማትም ሆነ ለኅብትም አስቸጋሪዎች ናቸው፡፡ የሌሎን አስተያየት ለመቀበል ፈቃደኞች አይሆኑም፡፡ የሌሎች ሰዎችን ፍላጎት ለመረዳት አይችሉም፡፡ እንዲሁም ለሌሎች ደንታ የላቸውም፡፡ እነርሱ ግለኝነት የሚያጠቃቸውና በርህራሄ ለመጋዘን ያቅታቸዋል፡፡
እግዚአብሔር ልባችንን እንዲያለሰልስና ሩህሩህ እንድንሆን እንዲረዳን በእርሱ ድምፅና ለእርሱ መንካት ስሜት እንዲኖረን በመጨከን እግዚአብሔር እንፈልግ፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ነገሮች አንተ በፈለከው መንገድ ሳይሄዱ ሲቀሩ እግዚአብሔርን በጥሩ ባሕሪ ታመን፡፡