እግዚአብሔር በመከራችን አይከብርም

እግዚአብሔር በመከራችን አይከብርም

አሳባችሁም በላይ ባለው ላይ እንጂ በምድራዊ ነገር ላይ አይሁን፡፡ – ቆላ 3፡2

ብዙ ክስስቲያኖች እግዚአብሔር መከራን እንዲቀበሉ ይፈልጋል ብለው በውሸት ሀሳብ ስር ይኖራሉ፡፡ይሄ ደግሞ በማያቋርጥ ሁኔታ እየተጎዳሁ ነው የሚል ስሜትን ይፈጥራል።

መከራ የሚቀር ጉዳይ አይደለም ነገር ግን እግዚአብሔር በመከራችን አይደሰትም፡፡በመከራችን ወቅት መልካም ምልከታ ሲኖረን እግዚአብሔርን ይባርከዋል እናም ባለድል እንድንሆን ይፈልጋል!

ታዲያ ለምንድነው መራር፣ተናዳጅ እና የቆሰለ ወይም የደበረው መሆንን የምንመርጠው?

አንድ የተረጋገጠ በትክክለኛ አስተሳሰብ መከራን ማሸነፊያ መንገድ አለ ፡አዕምሯችሁን በላይ ባለው ነገር ላይ እንዲያተኩር ፣አተኩሮ እንዲቀጥል አድርጉ እንጂ በምድር ባለው ላይእንዲያተኩር አታድርጉ፡፡በትክክለኛ አስተሳሰብ የታጠቃችሁ መሆን አለባችሁ ያለዚያ በከባድ ወቅት እጅ ትሰጣላችሁ፡፡

አዕምሯችሁን እንዲያተኩር አድርጉና ከተጎጂነት ወደ አሸናፊነት መለወጥ ፈጣን ሂደት እንደማይኖረው እወቁ፡፡ጊዜን ቢወስድም ልምምዳችሁ አጠንክሮ ተመሳሳይ ጦርነት ያለባቸውን ሌሎችን እንድትረዱ ያስችላችኋል፡፡

ስለወደፊታችሁ ጓጉ እናም ከእግዚአብሔር ጋር በሆነ ነገር ውስጥ ማለፍ ማለት በሌላኛው በኩል ከእናንተ ከማይወሰድ ድል ጋር መውጣት ማለት እንደሆነ እወቁ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ የተጎጂነት ስሜትን ለማሸነፍ እርዳታህን እፈልጋለሁ፡፡ትክክለኛው አስተሳሰብ ይኖረኝ ዘንድ አዕምሮዬን በላይ ያለው ላይ ማድረግን ጥሩ ስሜት እንዲኖረኝ ስል እመርጣለሁ፡፡በውስጤ ባለው የአንተ ሀሳብ እና እውነት ማሸነፍ እንደምችል አውቃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon