እግዚአብሔር በር ይዘጋል ይከፍታል

እግዚአብሔር በር ይዘጋል ይከፍታል

እንዲህ ብላህ ጻፍ፡- የዳዊት መክፈቻ ያለው ፤ የሚከፍት ፣ የሚዘጋም የሌለ ፣ የሚዘጋ ፣ የሚከፍትም የሌለ … – ራዕይ 3፡7

ከእግዚአብሔር መስማት አለመስማታችንን በእርግጠኝነት ማወቅ የምንፈልግበት ወሳኝ ጊዜዎች አሉ፡፡ ከስሜታችን አንጻር የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማት ቀላል ይመስላል፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ማንም ሊዘጋው የማይችል የእድል በሮችን ይከፍታል ፤ መክፈት የማንችለውንም በር ይዘጋል፡፡

በሕይወት የምፈለጋቸውን ነገሮች ለማግኘት በርካታ አመታትን አሳልፌያለሁ፡፡ ውጤቱም ድካም እና ብስጭት ብቻ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ስንደገፍ በእርሱ ትክክለኛ ሰዓት ሞገሱን ይሰጠንና ነገሮችን ያቀልልናል፡፡ በአንድ ጊዜ አንድ እርምጃ ያራምደናል፡፡ በተሳሳተ አቅጣጫ አንድ እርምጃ ስንጓዝ ብዙም ሳንርቅ ተመለሱ ይለናል፡፡

ሀሳቡ ከሀሳባችሁ በላይ መሆኑን ተገንዘቡ፡፡ መጨረሻውን ከመጀመሪያው ያውቃል ፤ መንገዱም እርግጠኛ እና ቀጥ ያለ ነው ፡፡ ለእናንተ ትርጉም ያለውን ነገር ያውቃል እናም ያደርገዋል፡፡ እንዳትሳሳቱ ድመጹን ስሙ!


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆ በሕይወቴ ውስጥ ትክክለኛውን ደጅ ክፈትልኝ ፤ ትክክለኛ ያልሆኑትን ዝጋ፡፡ ምንም ማድረግ እንዳለብኝ በማላውቅበት ጊዜ አንተን እንደምሰማ እና እንምከተልህ አምናሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon