እግዚአብሔር በሰዎች ይሰራል

እግዚአብሔር በሰዎች ይሰራል

እኛ ከጠበቅነው በላይ በመጀመሪያ ራሳቸውን ለጌታ ሰጡ፤ቀጥለውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ራሳቸውን ለእኛ ሰጡ፡፡ – 2 ኛ ቆሮ 8፡5

ንድ ጠዋት ከጌታ ጋር በግሌ የጥሞና ጊዜዬን እየወሰድኩ ሳለሁ ጌታን “ይሄንን ሁሉ በአለም ያለውን የህጻናት ርሀብ፣ህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣የጅምላ ጭፍጨፋ፣ፍርድ አልበኝነት፣ውድቀት እና ድህነት እያየህ ዝም ማለት እንዴት አስቻለሁ?” ብዬ ጠየቅኩት፡፡

ይሄንን ያልኩት በማማረር ወይም ታማኝነቱን በመጠራጠር አይደለም፡፡ዝምብዬ ጠየቅኩ እንጂ እንዲያውም መልስ አገኛለሁ ብዬ መጠበቄን እራሱ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡በፍጥነት ግን መልሱ መጣ፡” የምሰራው በሰዎች ነው፡፡ህዝቤ ተነስቶ አንድ ነገር እስኪያደርግ ድረስ እየጠበቅኩ ነው፡፡” አለኝ፡፡

እኔ እና እናንተ የክርስቶስ አካል የሚባል የአንድ ጦር አካል ነን፤እናም ይሄንን አለም ለመለወጥ እያንዳንዱ የራሱን ድርሻ ሊሰራ ይገባዋል፡፡እግዚአብሔር በእኛ መስራት ይፈልጋል፤ ለዛም ነው ፍቅርን ለብሰን ስራ እንድንሰራ የጠራን፡፡

በሁለተኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ላይ ጳውሎስ በመቄዶኒያ ያሉት አብያተ ክርስቲያናት እንዴት እንደሰጡ ሲናገር አስቀድመው እራሳቸውን ለጌታ እና ለእኛም(ወኪሎቹ) በእግዚአብሔር ፈቃድ (የግል ፍላጎቶቻቸውን ሙሉ በሙሉ በመተው በእግዚአብሔር ፈቃድ ለመመራት ሲሉ ራሳቸውን ለእኛ አሳልፈው በመስጠት ከሚችሉት በላይ ሰጡ)…ይላል፡፡

ይሄ እኔን በጣም ያስደንቀኛል ምክንያቱም የሰጡት ገንዘባቸውን ብቻ አይደለም ራሳቸውንም ጭምር እንጂ፡፡እግዚአብሔር እኛንም የጠራን በተመሳሳይ መንገድ እንድንኖር ነው፡፡አንድ ለእግዚአብሔር የሚሰራ ሰው ጥልቅ ለውጥ ለማምጣት አቅሙ አለው! ታዲያ እንዴት ነው ዛሬ ራሳችሁን ለጌታ አሳልፋችሁ በመስጠት ወኪሉ ለመሆን ያሰባችሁት?


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ በእኔ እንድትሰራ እጋብዝሀለሁ፡፡አለምን ለመለወጥ ትጠቀምብኝ ዘንድ እራስ ወዳድነትን ጥዬ ፍቅርን ለማንሳት እመርጣለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon