እግዚአብሔር በቀስታ ይመራናል

እግዚአብሔር በቀስታ ይመራናል

መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፤ ጠቦቶቹን በክንዱ ይሰበስባል፤ በዕቅፉም ይይዛቸዋል፤ የሚያጠቡትንም በጥንቃቄ ይመራል። (ኢሳይያስ 40:11)

እግዚአብሔር ሲናገረን እና ሲመራን አይጮኽብንም ወይም ወደሚፈልግበት አቅጣጫ አይገፋንም ። በፍጹም፣ እርሱ እንደ የዋህ እረኛ ወደ ለመለመ መስክ እንድንከተለው እየጋበዘን ይመራናል። ድምፁን በቶሎ ወደምንለይበት በጣም ዝቅተኛ በሆነ ማንቂያ እንኳን“ጌታ ሆይ፣ እዚህ ምን ትላለህ?” ብለን እንድንጠይቅ በቂ የሆነበት ደረጃ ላይ እንድንደርስ ይፈልጋል። እያደረግነው ያለነውን ነገር እንድንለውጥ ሲመራን በተሰማንበትቅጽበት በፍጥነት እሱን መታዘዝ አለብን። አንድ ነገርእያደረግን ስለዚያ ነገር ሰላም እንዳጣን ከተሰማን ቆም ብለን የእርሱንምሪት ለማግኘት እግዚአብሔርን መፈለግ አለብን።

ምሳሌ 3፥6 በመንገዶቻችን ሁሉለእግዚአብሔርእውቅና የምንሰጥ ከሆነ መንገዶቻችንን ያቀናል ይላል። በቀላሉ ለእግዚአብሔር እውቅና መስጠት ማለት ስለ እያንዳንዱ እንቅስቃሴአችን ምን እንደሚያስብ በመጠንቀቅ የሚገባውን ክብር መስጠት፣በቂ የሆነ የአክብሮት ፍርሃት ማሳየትና መፍራት ማለት ነው።

እያንዳንዱን ቀን ለመጀመር ጥሩው መንገድ መጸለይ ነው። “ጌታ ሆይ፣የምታስበው ነገር ይገደኛል። ደግሞም እንዳደርግ የማትፈልጋቸውን ነገሮችእያደርግኩ መገኘት አልፈልግም ። ዛሬ አንዳች እንዳደርገው የማትፈልገውን ነገር ማድረግ ጀምሬ እንደሆነ፣እንዳቆመው፣ እንድርቀው እና በምትኩ ፈቃድህን እንዳደርገው እባክህ ምን እንደ ሆነ አሳየኝ። አሜን ”


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ ከምንም ነገር በላይ እግዚአብሔር ስለሚያስበው ነገር አብልጠህ አስብ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon