እግዚአብሔር በተናጠል ይናገረናል

እግዚአብሔር በተናጠል ይናገረናል

ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዘወር ብትል ጆሮህ ከኋላህ፣ “መንገዱ ይህ ነው፤ በእርሱ ሂድ” የሚል ድምፅ ይሰማል። (ኢሳይያስ 30:21)

እግዚአብሔር ለእኛ የሚናገርበት አንዱ ምክንያት ጥሩ ምርጫዎችን እናደርግ ዘንድ በመልካም እና በክፉ መካከል ያለውን ልዩነት እንድናውቅ እኛን ለመርዳት ነው። አንዳንድ ነገሮች ለአንድ ሰው የተሳሳቱ ሆነው ለሌላው ትክክል ሊሆኑ ይችላሉ፤ ወይም ደግሞ በተቃራኒው፤ ስለሆነም ሁላችንም ከእግዚአብሔር ለየግላችን መመሪያ ያስፈልገናል። በእርግጥ የተወሰኑ ትክክል እና ስህተት የሚባሉት አጠቃላይ መመሪያዎች ለሁሉም ሰው ተፈጻሚ ይሆናሉ፤ ለምሳሌ፦ ልክ እንደሌሎቹ ብዙ ነገሮች ሁሉ ውሸት፣ ማጭበርበር እና መስረቅ ስህተት እንደሆኑ ሁላችንም እናውቃለን። ነገር ግን በግለሰብ ደረጃ ለእኛ የተለዩ ነገሮችም አሉ። ልጄ በጉዞ ላይ ነበር እና አንድ ቀን ለማራዘም አቅዶ ነበር፤ ግን ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነቃ ስለ መቆየት ሰላም ስላልተሰማው ወደ ቤቱ ተመለሰ። እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው የተለያዩ እና ልዩ እቅዶች አሉት፤ ደግሞም እኛ ስለራሳችን እንኳን የማናውቃቸውን አንዳንድ ነገሮችን ያውቃል።

በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ሁሉ የሚያደርጉትን አንድ ነገር እግዚአብሔር ለምን እኛ እንዳናደርግ እንደሚነግረን ላይገባን ይችላል፤ ነገር ግን ልባችን ለስላሳ ከሆነ ለምን እንደሆን ባይገባንም እንኳ እሱን እናምናለን ደግሞም እንታዘዛለን ። ዋናው ነገር እሱ ከሚጠይቀን ወይም ከሚጠብቅብን ነገር ሁሉ በስተጀርባ ያለውን ምክንያት የግድ ማወቅ የለብንም፤ እንዲሁ ድምፁን ለመስማት እና ለመታዘዝ መማር ነው የሚያስፈልገን። ለጦርነት ስልጠና ላይ ያሉ ወታደሮች አንዳንድ ጊዜ አስቂኝ ልምዶችን እንዲያደርጉ ይጠየቃሉ፣ ትርጉም የማይሰጡ የሚመስሉ ነገሮችን ማለት ነው ። ፈጥነው እነዚያን ነገሮች ማድረግ ይማራሉ ደግሞም ባይረዱም እንኳ በፍጥነት እና ያለምንም ጥያቄ ትዕዛዞቹን ይታዘዛሉ። በጦርነቱ ግንባር ላይ ከሆኑ እና መሪዎቻቸው ትእዛዝ ከሰጡ ቆም ብለው “ለምን?” ብለው ቢጠይቁ ሊገደሉ ይችላሉ ። በተመሳሳይ ሁኔታ፣ እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥ የእርሱን የፍቅር መመሪያ እንድናምን እና ያለ መዘግየት እና ያለ ምንም ጥያቄ እንድንታዘዘው ይፈልጋል።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ በማትረዳበት ጊዜም እንኳ ቢሆን የእግዚአብሔርን ድምፅ ታዘዝ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon