እግዚአብሔር በአምልኮ ውስጥ ይናገረናል

እግዚአብሔር በአምልኮ ውስጥ ይናገረናል

ኑ እንስገድ ለእርሱም እንገዛ በእርሱ ባደረገን በእግዚአብሔር ፊት እንባረክ፡፡ መዝ፡ 95÷6

እንደ እምነት አምልኮ እግዚአብሔር ለእኛ የሚናገርበት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ አምልኮ እንደዚህ ነው ብሎ መተርጎም ያስቸግራል፡፡ አምልኮ አብዛኛውን ጊዜ ስለ አምልኮ ጉዳይ እንጂ ስላደረገንልን ነገር ላይ የሚያተኩር አይደለም፡፡ እውነተኛ አምልኮ ከውስጥ ማንነታችን ውስጥ የሚወጣ፣ በጣም ውድና ደስ የሚያሰኝ ስለእግዚአብሔር ሚሰማትን በተመስጦ ውስጥ ሆነን በቃላት ለመግለፅ የምናሳየው ጥረት ነው፡፡ ከውስጠኛው ልባችን በኃይል የሚወጣ ለእግዚአብሔር ያለን ጥልቅ ፍቅር፣ ምሥጋና ተመስጦ በሰው ቋንቋ ቃላት ለመግለፅ የሚቅት የለውም፡፡ በእርግጥ አምልኮ ግላዊና የቀረቤታ ጉዳይ ስለሆነ እንዲህና እንዲህ ነው በማለት በገዛ ቃሎቻችን ገድቦ ማስቀመጥ ወይም መተርጎም የሚያዳግት ሊሆን ይችላል፡፡

አምልኮ ዝማሬን ከመዘመር እጅግ ያለፈ ጉዳይ ነው፡፡ በእርግጥ እውነተኛ አምልኮ ከሁሉ ቀድሞ በመጀመሪያ የአእምሮና የልብ ሁኔታ መጣመር ነው፡፡ በግላችን ያለዝማሬ ማምለክ እንችላለን፡፡ አምልኮ የሚወሰደው ከልባችን ሆኖ ሃሣባችን በመቆጣጠር ከዚያ በአእምሮ ተቀናብሮ በአንደበትና በሰውነታችን ይገለጣል፡፡ ልባችን ለእግዚአብሔር በምሥጋና ሲሞላ ልንዘምር፣ ልንደንስ፣ ልናጨበጭብ ወይ ደግሞ እጃችንን ወደ ላይ አንስተን እናመልካለን፡፡ እንዲሁም ዝግና ዝም ብለን በእግዚአብሔር ፊት ፀጥ በማለት ማምለክ እንችላለን፡፡ ከዚያም ባለፈ መስዋዕት የማቅረብ ፍላጎት ኖሮን በውጭ በሚታይ የእግዚአብሔር የፍቅር መግለጫ ማሳየትና ማምለክ እንችላለን፡፡ ነገር ግን እነዚህ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ከእውነተኛ ልብ ካልሆነና ዝም ብሎ ውጫዊ ድርጊት ከሆነ በእግዚአብሔር ፊት እንደ ደንብና ትርጉም የሌለው ይሆናል፡፡

እግዚአብሔርን ከልብህ እንድታመልከው እኔ ዛሬ አበረታታሃለሁ፡፡ ይህንን የምታደርገው ደግሞ እግዚአብሔርን ስለምትወድ ነው፡፡ በአምልኮ ውስጥ እያለ እግዚአብሔር ብነገርህ ደግሞ ብዙም አታድንቅ ምክንያቱም እግዚአብሔር በእውነት ለሚያመልኩት ይናገራልና፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- እግዚአብሔርን ለማንነቱ የሚገባውን ምሥጋና ባለማቅረብ ከልብህ አምልከው፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon