እግዚአብሔር ብርታትንና መጽናናትን

እግዚአብሔር ብርታትንና መጽናናትን

« …የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ» (2ኛቆሮ.1፡3)

እኛ ሁላችንም ተቀባይነትን ማግኘትን እንፈልጋለን፤ መናቅን ወይም መተውን አንፈልግም። እኔ ብቸኝነትን፣ የመገለልን ስሜትና ከመናቅ ስሜት የሚመጣውን የስሜት ህመም እጅግ እጠላዋለሁ፣ በትክክል ይህንን ለብዙ ዓመታት ተለማምጄዋለሁ፣ ማወቅ ብቻ ሳይሆን ለዚህ ብዬ ማንኛውንም ነገር ላድርግ እችላለሁ። እግዚእብሔር ይመስገን አሁን ሁሉም ነገር ተቀይሯል። ከብዙ ዓመታት በፊት የድሮው የመገፋት ዓይነት ህመም አንዳንድ ጊዜ ያጋጥመኝ ነበር። በህጻንነት ዘመኔ በጣም የጎዳኝን አንድ ሰው አገኘሁት። ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ ምንም የእኔ ስህተት ባልሆነ ነገር እኔ እነቀፍ ነበርና ይህ ሰው በእኔ ላይ ምንም ፍላጎት ወይም ድብቅ ዓላማ እንደሌለው የሚገልጥ ግልጥ መልዕክት ተቀበልኩኝ።

እኔ ራሴን ማታለል ወይም ራሴን ይቅር የማለት ስሜት እንዲሰማኝ ፈለግሁ፣ ነገር በዚህ ፈንታ ወዲያውኑ የመንፈስ ቅዱስን ማጽናናት እንዲሰጠኝ ወደ እግዚአብሔር ጸለይኩኝ። እርሱ የቆሰለውን ስሜቶችን እንዲፈውሳቸውና ኢየሱስ ያድርገው እንደነበር ሁኔታዎችን በትክክል መያዝ እንድችል እንዲረዳኝ ጸለይኩኝ። ከዚያም የሆነ ሙቀት በላዬ ላይ ሲያልፍ ተሰማኝ፣ አብዛኛውን ህወቴን በእርካታ የሚያጥለቀልቅ ዘይት በቆሰለው ቁስሎቼ ላይ ፈሰሰ።እግዚአብሔር ይህንን የጎዳኝን ሰው ይቅር ይላው ዘንድ ጸለይኩኝ፣ እንዲሁም ወደ አዕምሮዬ «የተጎዱ ሰዎች ሰውን ይጎዳሉ» እንዲህ የሚል ቃል አመጣ። የእርሱ የቀረበ የግል ምላሽ ለቆሰለው መንፈሴ ፈውስን አመጣልኝ።

እግዚአብሔር የመጽናናት ሁሉ፣ የርህርሄ ሁሉና የብርታት ሁሉ አምላክ ነው። እባክህ የምመክርህ ነገር ከእርሱ ጋር ያለህን የጠበቀ የግል ህብረት እንድታጎለብትና እንድታጠነክር ማንኛውንም ነገር አድርግ። ምክንያቱም ይህ የእርሱን ድምጽ ለመስማት፣ ከእርሱም መጽናናትንና ፈውስን የምትቀበልበትና በእርሱ ማበረታታትና እንክብካቤ ልትጠነክርበት የምትችልበት አውድ ስለሆነ ነው።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ እግዚአብሔር መጽናናት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ያውቃል፣ መንፈስ ቅዱስ ይህንን እንዳደርግልህ ወደ አንተ ልኮታል።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon