እግዚአብሔር ብቁና ጽኑ ነዉ

እግዚአብሔር ብቁና ጽኑ ነዉ

ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንት፣ ዛሬም ለዘላለምም ያዉ ነዉ፡፡ – ዕብ 13:8

ባለቤቴ ዳዊት በጽናት በሰላምና በመረጋጋት የሚኖሩ ሰዎች ትልቁ ምሳሌ ይሆናል፡፡ እርሱ ከኢየሱስ ስሞች አንዱ ስለሆነዉ ዓለት ዘወትር ያሳስበኛል፡፡

ልክ እንደማይንቀሳቀስ ዓለት ኢየሱስ ሳይለወጥ ይኖራል፡፡ የዕብራዊያን ጸሓፊ እርሱ ትናንትና ዛሬም ለዘላለምም ያዉ እንደሆነ ጽፎአል፡፡

ዳዊት እንደለዉ ዓይነት ጽኑ ሰላምና መረጋጋት ዉስጥ ለመኖር እታገል ነበር፡፡ አንድ ቀን እደሰትና በሚቀጥለዉ ደግም እከፋለሁ፡፡ በመጨረሻም ዳዊትን በሰላም የተሞላ ያደረገዉ ምን እንደሆነ ልብ አልኩኝ፤ እርሱ በማይለወጠዉ ጌታ አምኗል፡፡ ምን ይከሰት ምንም ይሁን እግዚአብሔር ያዉ ሆኖ እንደሚኖር አዉቋል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን ጌታ የእኛ እግዝአብሔር ሁሌ ከእኛ ጋር ያለዉ ሐያል እንደሆነ ነዉ (ት. ሶፎ 3፡17ን ተመልከት)፡፡ እኛ በማይለወጠዉ ስሙ እንድናሸንፍና እንድንኖር በቃሉና በመንፈሱ ሊረዳን ሐያል ነዉ፡፡

አምላካችን ብቁና ጽኑ ነዉ፡፡ ታዲያ ዛሬ ለምን አታምኑትም? ምንም ቢፈጠር እርሱ የማይለወጥና ያዉ መሆኑን ስታስተዉል ህይወትህን በእርሱ አለመለወጥ ላይ ስትመሰርት፤ እርሱ ለአንተ ሊሰጥህ የሚጓጓዉን የረጋ ሀሴት ታገኛለህ፡፡ ለምን ዛሬ አትጀምሩም?


የጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ አንተ ብቁና ጽኑ ነህ! በዚህ ህይወት ብቸኛዉ ጽኑ አንተ ነህ፡፡ ምንም ቢከሰት ባንተ እንደምታመንና በማይለዋወጠዉ ማንነትህ እንደማምን አዉቃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon