እግዚአብሔር ብቸኛው ዘላቂ ምንጭ ነው

በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤የልብህንም መሻት ይሰጥሃል፡፡ – መዝ 37፡4

ሰው እንደመሆናችን በእግዚአብሔር የተፈጠርነው ደስተኛ እንድንሆን እና ስለራሳችን ጥሩ እንዲሰማን ነው፡፡የግድ ስለራሳችን ጥሩ ሊሰማን ይገባል አለበለዚያ የምንፈልገውን ጥሩ ስሜት ለማግኘት ስንል ጤናማ ያልሆነ እና ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ባህሪ እናዳብራለን፡፡

አስቡበት፡፡የዕጽ ሱሰኛ የሆነ አንድ ሰው ምናልባትም መጠቀም የጀመረው ህመሙ ከአቅሙ በላይ ስለሆነበት ለጊዜውም ቢሆን ሊያስወግደው ፈልጎ ሊሆን ይችላል፡፡ስለመጠጥም ሆነ ምግብን ለምቾት መጠቀም ተመሳሳይ ነው፡፡ከውስጣችን ጥሩ ስሜቶች ማግኘት ካልቻልን በውጫዊ መንገድ ልንፈጥራቸው እንጥራለን፡፡

እግዚአብሔር የፈጠረን በዛ መንገድ ስለሆነ ሊያረካን የሚችለው ብቸኛው ነገር እርሱ ነው፡፡ስለራሳችን ጥሩ እንዲሰማን ከእግዚአብሔር ይልቅ ወደሌላ ነገር ስንሄድ እውነተኛን ነገር በሌላ ርካሽ ነገር እየተካነው ነው፡፡

ዛሬ ያለባችሁ የስሜት ክፍተት ምንም ሆነ ምን እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ ሊሞላቸው እንደሚችል ዕወቁ፡፡የህይወታችሁ ዘላቂ ምንጭ እርሱ ብቻ ነው፡፡ዛሬ ወደ እርሱ ሂዱ ሊያረካችሁ የሚችለው እርሱ ብቻ ነው፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ርካሽ መተኪያዎችን እያሳደድሁ ጊዜዬን ማቃጠል አልፈልግም፡፡አንተ ብቻ ነህ የምታረካኝ፡፡የየቀኑን እውነተኛ ደስታዬን እና እርካታዬን በአንተ እና በአንተ ብቻ እንዴት እንደማገኝ አሳየኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon