እግዚአብሔር ተራ በተራ ገመዳችሁን እየፈታ ነው

ጌታ ልባችሁን ወደ እግዚአብሔር ፍቅርና ወደ ክርስቶስ ጽናት ይምራው። – 2 ኛተሰሎ 3፡5

ህይወታችሁን ልክ ተበጣጥሶ እንደተሳሰረ ገመድ ተመልከቱት። እያንዳንዱ ገመድም የራሱ ቀለም አለው ፤ እያንዳንዱ ገመድም ችግርን ይገልጻል። እያንዳንዱን ገመድ ማፍታታትና ቀጥ ማድረግም የተወሰነ ግዜ እና ስራ ይጠይቃል። እነዚህን ሁሉ ገመድ ለማሰር ግዜ እንደወደ ሁሉ ለማቃናትም ግዜ ይወስዳል።

አሁን ባለንበት  በዚህ ፈጣን ዓለም ሰዎች ከአንዱ ነገር ጫፍ ወደሌላ ነገር ጫፍ  ይዘላሉ ነገር ገን እግዚያብሄር አይቸኩልም።  መቼም ተስፋ አይቆርጥም ፣ ትዕግስትም አያጣም፡፡ ስለ አንድ ነገር በእኛ ውስጥ ይሰራና እንድናየው ጊዜ ይሰጠናል ነገርግን በጣም ብዙ ጊዜ አይሰጠንም። ከዚያም ደግሞ ተመልሶ ይመጣና በእኛ ውስጥ ሌላ ነገር ላይ ይሰራል፡፡ የተሳሰሩ ገመዶቻችን አንድ በአንድ እስኪፈቱ ድረስ ይህንን ማድረጉን ይቀጥላል።

አንዳንድ ግዜ ምንም ለውጥ ያመጣችሁ ባይመስላችሁ እግዚአብሔር አንድ በአንድ እናንተ ላይ እየሰራ ስለሆነ ነው። የርሱ ትዕግስትም በናንተ ይደግ እንደዚህ ከሆነ በቅርቡ በህይወታችሁ ውስጥ ድልን ታያላችሁ ፤ ለረጀም ግዜም ስትፈልጉት የነበረውን ነፃነት ታገኛላችሁ።

ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ የህይወቴን ውጣውረዶች አስወግደህ ቀጥ ያለ ስለምታደርገው አመሰግንሃለሁ፡፡በህይወቴ ስትሰራ በትዕግስት እንድጠብቅ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon