እግዚአብሔር ይባርክህ፤ይጠብቅህም፤እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፤ይራራልህም(መልካም፣ምህረትን የተሞላ እና ሞገስን የሚሰጥ)፤እግዚአብሔር ፊቱን ይመልስልህ(ይቀበልህ)፤ሰላሙንም ይስጥህ፡፡ – ዘሁ 6፡24-26
ለሰዎች አበረታች ንግግር መናገር አለብን፡፡በዘሁልቁ 6፡24-26 የተጻፈውን ቡራኬ ትንሳኤን እንዲያገኝ ማድረግ አለብን፡፡እግዚአብሔር ይባርክህ፤ይጠብቅህም፤እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፤ይራራልህም (መልካም፣ምህረትን የተሞላ እና ሞገስን የሚሰጥ)፤እግዚአብሔር ፊቱን ይመልስልህ(ይቀበልህ)፤ሰላሙንም ይስጥህ…
በሌላ ቃል እግዚአብሔር ፈገግ እያለላችሁ ነው፡፡አስቡበት፡፡ለአንድ ሰው ፈገግ ባላችሁ ቁጥር እያላችሁ ያላችሁት “ተቀብዬሀለሁ፣ደስ ትላለህ፤ጥሩ ነህ ነው፡፡”
እግዚአብሔር መቀበል ብቻ ሳይሆን በርስዎ ፈገግ እያለ ነው። ይወዳችኋል! ይሄ ምምም ነገር እንዳያወጣው ሆኖ በልባችሁ ውስጥ በደንብ ሊተከል ይገባዋል፡፡
በእግዚአብሔር ፍቅር ስትተከሉ በእምነት እንድትቆሙና እርሱን በመታዘዝ መራመድ እንድትጀምሩ ይረዳችኋል፡፡በራሳችሁ መልካም ስራዎችን ለመስራት እየጣራችሁ ቀድማችሁት መሄድ ግን አትችሉም፡፡በክርስቶስ ማን እንደሆናችሁ እንድታውቁ ቃሉን ማወቅ አለባችሁ፡፡
መዝ.18፡19 ላይ ዳዊት “እግዚአብሔር ደስ ተሰኝቶብኛልና” ይላል፡፡ ዳዊት ፍጹም አልነበረም ነገር ግን እግዚአብሔር በእርሱ ደስ እንደተሰኘበት ያውቃል፡፡እግዚአብሔር በእናንተም ደስ ይለዋል፡፡ይሄንን እውነት ወደ ውስጣችሁ አስገቡት፡፡በእናንተ ፈገግ እያለ ነው እናም በጣም ይወዳችኋል፡፡እግዚብሔር ተቀብሏችኋል!
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ ስለተቀበልከኝ እና ስለምትወደኝ አመሰግናለሁ፡፡በእኔ ላይ ፈገግ ስላልክ አመሰግናለሁ፡፡ፍቅርህ ህይወቴን ቀይሮታል በአንተ እያደግሁ ስሄድም እንዲሁ እንደሚቀጥል አውቃለሁ፡፡