እግዚአብሔር ነፍስህን ይመልሳል (ያድሳል)

እግዚአብሔር ነፍስህን ይመልሳል (ያድሳል)

«…ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ» (መዝ.23፡3)።

ለብዙ ጊዜያት በህይወቴ ውስጥ እንዲሆኑ የማልፈልገው ማንኛውም ነገር ሁሉ ሲገጥመኝ እቃወም ነበር። ምክንያቱም ይህ የማልፈልገው ነገር ከሰይጣን ነው ብዬ አስብ ስለነበር። ይህንን የምለው «ተቃዋሚዬ» ሙሉ በሙሉ ተስፋ እስኪቆርጥና እስኪደክም ድረስ እቃወመዋለሁ። ነገር ግን ከዚያ በኋላ የተረዳሁት ነገር ቢኖር ብዙ ልቃወማቸው የሞከርኳቸው ነገሮች ከእግዚአብሔር ነበሩ። ብዙ እኔ የማልፈልጋቸው ነገሮች ወይም የማልወዳቸው ነገሮች እግዚአብሔር ለእድገቴና ለብስለቴ ፈቅዶ ወደ እኔ ያመጣቸው ነገሮች ነበሩ።

የዕብራውያን ጸሐፊ ሲናገር እኛ ለእግዚእበሔር ቅጣት (ዲሲፕሊን) ራሳችንን ማስገዛት አለብን። እርሱ ስከሚወደን ብቻ ይቀጣናል። እግዚአብሔር ለአንተ መልካም እንደሆን አስቦ የሚሠራውን (ያቀደውን) ለመቃወም አትሞክር። እግዚአብሔር በአንተ የጠለቀና ሙሉ የሆነ ነገር እንዲሠራ ጠይቀው (ጸልይ)። እንደዚህ ሲሆን እርሱ እንድትሆን የሚፈልገውን መሆን ትችላለህ። እርሱ እንድታደርገው የሚፈልገውን ታደርጋለህ፤ እንዲሁም እንዲኖርህ የሚፈልገውን እንዲኖርህ በጸሎት እርሱን ጠይቀው። ማንኛውንም ነገር አስቸጋሪና ጎጂ ሆኖብኝ ስቃወም በነበርኩበት ዓመታት ውስጥ እኔ በቀላሉ የምለው እውነት በመንፈሳዊ ህይወቴ አላደኩም ነበርኩ። እኔ ተደጋጋሚ /ተመሳሳይ/ አሮጌ ተራራዬን /ችግሬን/ ደግሜ ደጋግሜ መዞር ብቻ ሆነብኝ። በመጨረሻም እኔ ጉዳቶች ለማስወገድ ስጥር እንደነበር አረጋገጥኩ። ነገር ግን አሁንም ጉዳቶች ነበሩብኝ አብሮን የሚቆይ ጉዳት (ህመም) ከሚለውጥ ህመም (ጉዳት) የበለጠ ክፉ ነገር በእኛ ላይ የሚሆንበት መንገድ ነው።

የእኛ ማንነት ነፍሳችን (አዕምሮ፣ ፈቃድና ስሜት) ናት። ነገር ግን ብዙውን ጊዜ በዓለም ውስጥ ባሉን ልምምዶች እየቆሰልን /እየተጎዳን/ እንኖራለን። የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ግን እኛ በውስጣችን ካለው ከመንፈስ ቅዱስ ሥራ ጋር ከተባበርን ነፍሳችንን ያድሰዋል። እኔ ምንም ሰላምና ደስታ የሌለበት የተሰበረ ነፍስ ነበረኝ። ነገር ግን እግዚአብሔር ፈወሰኝ። ለአንተም እንዲሁ በተመሳሳይ ይሰራል።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ ለእግዚአብሔር ነፍስህን የተከፈተ አድርግ እናም ማንኛውንም ቁስልህንና ጉዳቶችህን ይፈውሰዋል።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon