እግዚአብሔር ናፍቆትህን ያረካዋል

እግዚአብሔር ናፍቆትህን ያረካዋል

« … ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች። ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?» (መዝ. 42፡1-2)።

እኔ አጥብቄ እየወደድኩት እንኳን እግዚአብሔር ለእኔ ሊናገር እንደሚፈልግ ሳላውቅ ለብዙ ዓመታት ወደ ቤተ ክርስቲያን እሄድ ነበር። በእሁድ አምልኮ ላይ እየተሳተፍኩ፣ የቤተክርስቲን ኃይማኖታዊ ህግና ሥርዓት እየጠበቅሁ በየበዓላቱም እመላለስ ነበር። በዚያን ሰዓት ለማድረግ የማውቀውን ሁሉ አደርግ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን ለምንናፍቀው ናፍቆት ሊያረካኝ ህ በቂ አልነበረም።

እኔ በቤተክርስቲያን ፕሮግራሞች ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዳንዷን ደቂቃ ለማሳለፍ እችል ነበር ነገር ግን እነዚያ ነገሮች ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ካለኝ የጠበቀ ህብረት ከሚመጣ እርካታ ሊያረካኝ አልቻለም። ለእርሱ ያለፈውን ዘመኔን ለመንገርና እርሱ ደግሞ ስለወደፊቱ ህይወቴ የሚናገረኝን ለመስማት እፈልግ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር በቀጥታ ሊናገረኝ እንደሚፈልግ ማንም አላስተማረኝም ነበር። አንድም ሰው ስለመንፈሳዊ ናፍቆቴ መፍትሔ የሚሆነውን ሊያቀርብልኝ አልቻለም።

መጽሐፍ ቅዱስ በማንበብ ውስጥ እግዚአብሔር ሊናገረኝ እንደሚፈልግና በእርሱ ህልውና ናፍቆታችንን ሊያረካናከእኛ ጋር ህብረት ሊያደርግ እንደሚፈልግ ተማርኩኝ። እርሱ ለህይወታችን ዕቅድ አለው። ይህ ዕቅድ ወደ ሰላምና እርካታ ይመራናል። እንዲሁም ስለእርሱ እውቀትና መረዳት የእርሱን ፈቃድ በመለኮታዊ ምሪት ውስጥ እንድናገኝ የሚፈልግ መሆኑ ነው።

እግዚአብሔር ስለእያንዳንዱ አንተ ስለምታስበው ነገር የሚያስብልህና የእርሱ ዕቅድ ደግሞ በእያንዳንዱ የህይወትህ ክፍል ውስጥ ሊሠራ ያስብልሃል። ይህን እውነት ማወቅና ማመን ኃይማኖታዊ ግዴታ ከመፈጸም ይልቅ አረማመዳችን ጀብዱ እንደሠራ ጀግና እንሚጓዘው ይሆናል።


ዛሬለአንተያለውየእግዚአብሔርቃል፡ ዛሬ ከእርሱ ጋር የምታሳልፈው የጥሞና ጊዜ በእርግጥ ጥሞና ይሆንልሃል። እረፍና እግዚአብሔር ለአንተ ሊያካፍል የሚፈልገውን ስማ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon