እግዚአብሔር አስጎብኚያችሁ እንዲሆን ፍቀዱ

ይህ አምላክ ከዘላለም እስከዘላለም አምላካችን ነውና፤እስከመጨረሻው የሚመራንም እርሱ ነው፡፡ – መዝ 48፡14

በዚህ ምድር ላይ ሲኖር ኢየሱስ መደረግ ያለበትን ትክክለኛውን ነገር ያውቅ ነበር ምክንያቱም አባቱ ሲያደርግ ያየውን ብቻ ነበር ያደርግ የነበረው፡፡እንደ ጌታችን በየቀኑ በትክክለኛው ጎዳና እንዲመራን ልናምነው እንችላለን፡፡

መዝ.48፡14 ሲናገር እግዚአብሔር እስከሞት ይመራናል! ከአንድ የኑሮ መስመር ወደ ሌላው የሚያደርሰን መሪ እንዳለን ማወቅ እንዴት ደስ የሚል ነገር ነው፡፡

ባለቤቴ ዴቭ እና እኔ አንድ አዲስ ቦታ ስንጎበኝ ብዙ ጊዜ አስጎብኚ እንቀጥራለን፡፡አንድ ጊዜ በራሳችን ለማየት ወሰንን ነገር ግን በፍጥነት ሙሉ በሙሉ ጊዜያችንን እያባከንን እንደሆነ ተረዳን፡፡አብዛኛውን የቀኑን ክፍል ጠፍተን በሚያሳዝን ሁኔታ መንገዳችንን ለማግኘት ስንፈልግ ነው ያሳለፍነው፡፡

አንዳንዴ ህይወትን ልክ ዴቭ እና እኔ ያንን ጉዞ ባየንበት መንገድ እንደምናየው አስባለሁ፡፡ሁልጊዜም ልምድ ያለውን የጉዞ መሪ መከተል በራስ እዚም እዚያም ከማለት ይልቅ ቀላል ነው፡፡በራሳችሁ መንገድ ከመሄድ ይልቅ አባታችሁ ሲያደርግ ያያችሁትን አድርጉ እናም እንዲመራችሁ ፍቀዱለት፡፡እግዚአብሔር እኛን ለመምራት ታማኝ ስለሆነ የእኛ እርሱን መከተል አስፈላጊነቱ ግልጽ ነው፡፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ህይወቴን የመንገድ መሪ እንደሌለው ጎብኚ ያለ እቅድ በራሴ መንገድ እየሄድኩ መኖር አልፈልግም፡፡አንተ ብቻ ነህ ምን ማድረግ እና እንዴት መኖር እንዳለብኝ ልታሳየኝ የምትችለው፡፡ስለዚህ በየዕለቱ የአንተን ምሪት ለመከተል መርጫለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon