እግዚአብሔር እንድናድግ ይረዳናል

እርስ በርሳችን እየተነሣሣንና እየተቀናናን በከንቱ አንመጣ፡፡ ገላ 5 26

የእያንዳንዱ ግለሰብ ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ኅብረትና ድምፅን የመስማት ችሎታ የተለያየ ነው፡፡ ስለዚህ ነፃ ሆነ ከእርሱ ጋር ኅብረት ማድረግ እርሱ በሚመራህ መንገድ ቀጥልበት፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የሚደረግ ኅብረት ዝም ብሎ የሆነ ጥረት ወይም የሆነ ነገር ለማከናወን የሚደረግ ልፋት ሳይሆን በቀላሉ ለእርሱ የመናገርና ድምፁን የመስማት ሂደት ነው፡፡ እኛ በደረስንበት የሕይወት ደረጃ ልክ እንጂ ከእኛ በሕይወት ልምምድና ተሞክሮ ልቆ ከሄዱት ጋር አይደለም እራሳችንን ማወዳደር ያለብን፡፡ ምክንያቱም ያኛው ግለሰብ ወደዛ የሕይወት ደረጃ ለመድረስና ግልፅ የሆነ የእግዚአብሔር ድምፅ ለመስማት ብዙ ዓመታት ፈጅዩበት ይሆናል፡፡ በመንፈሳዊ ጉዳይ እኛም ገና ያልበሰልን ለጋ ብንሆንም ወደፊት እንላሎች ወዲዚያ ልምምድ በመድረስ ስለምናድግ እራሳችንን ከሌሎች ጋር ከማወዳደር ባለንበት ደረጃና ልምድ ለእግዚአብሔር በመናገርና ከእርሱ በመስማት ወደ ፍጹምነት ለመምጣት በምናደርገው ሂደት እግዚአብሔር ይደሰታል፡፡ ምክንያቱም በዚህ መንገድ እየተማርን ስለምናደግ ነው፡፡

ከሌሎች ጋር እራስህን ስታወዳድር መንፈሣዊ እድገትን ያጨልማል፡፡ እግዚአብሔር በጥልቀት የሚያቅህና ለግልህ የሆነ ዕቅድ ለአንተ እድገት አለው፡፡ እግዚአብሔር አመጣጥህን፣ ምን ልማድ እንዳለህ፣ ቅር የሚያሰኝህን ሕመምህን ያውቃል፡፡ እንዲሁም አንተ አርሱን በፈለከው መጠን ሙሉ በሙሉ በሕይወትህ አስተማማኝ እንድትሆን የሚያደርግህ ምን መሥራት እንዳለበት ያውቃል፡፡

እኔ አራት ልጆች ሁሉ የተለያዩ ባሕሪ ያላቸው ሲሆን እኔም እነርሱ ከሆኑት ውጭ ሌላ ነገር እንዲሆኑ አልጠብቅም፡፡ እግዚአብሔርም ልክ እንደዛው በእኛ ጉዳይ ላይ የሆነውን እንድንሆን ይፈልጋል፡፡ አንተው እራስህ የራስህን ደስታና የደረስክበትን የመንፈሣዊ ዕድገት ደረጃ ባገኘው መረዳት ደስተኛ ሁን፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ልትደርስበት እየሄድክበት ባለው መንገድ ደስተኛ ሁን፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon