እግዚአብሔር እየተናገራችሁ ያለውን ስሙና ታዘዙ

እግዚአብሔር እየተናገራችሁ ያለውን ስሙና ታዘዙ

ታዲያ ለእነርሱም ሆነ ለልጆቻቸው ለዘላለም መልካም እንዲሆንላቸው፣እኔን እንዲፈሩና ሁልጊዜ ትእዛዞቼን ሁሉ እንዲጠብቁ እንደዚህ ያለ ልብ ቢኖራቸው ምናለ! – ዘዳ 5፡29

እግዚአብሔር የሚናገረው በአገልግሎት ላሉ መሪዎች ብቻ አይደለም፡፡ በሁሉም የህይወት መንገድ ላይ ላለ ከእርሱ ጋር የግል ግንኙነት ላለው ለሁሉም ሰው ይናገራል፡፡ ብዙ ሰዎች ከእግዚአብሔር ለመስማት አይጠባበቁም ነገር ግን እውነታው ለሁላችንም ይናገራል፡፡ ለእናንተ እየተናገራችሁ ነው፡፡

እርግጥ ነው ድምጹን እያዳመጣችሁ ካልሆነ ሰምታችሁ ልታደርጉት አትችሉም፡፡ መጽሀፍ ቅዱሳችሁን ስታነቡ ፣ በህልውናው ውስጥ ረጋ ብላችሁ ጊዜን ስትወስዱ እና በቋሚነት ከእርሱ ለመቀበል ልባችሁን ስታዘጋጁ ትሰሙታላችሁ፡፡ በዛ መንገድ ትዕዛዛቱን መከተል እና ህጎቹን መጠበቅ ትችላላችሁ፡፡

ዘዳግም 5፡29ን አንብቡ፡፡ ይህንን አረፍተ ነገር ሲናገር በእግዚአብሔር ድምጽ ውስጥ ከልብ መመንጨቱ አይሰማችሁም? ደህና እንድንሆን ትዕዛዛቱን እንድንጠብቅ ይፈልጋል፡፡ ስለደህንነታችን ይጠነቀቃል እናም እኛን መንከባከብ የሚችልበት ብቸኛው መንገድ የምንሰማው እና የምንታዘዘው ከሆነ ብቻ እንደሆነ ያውቃል፡፡

ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ያላችሁን ግንኙነት የህይወታችሁ ዘይቤ አድርጉትና በታማኝነት የቃሉ አድራጊ ሁኑ፡፡ዛሬ ጥበቡን ስሙና ተከተሉት፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ እየተናገርከኝ እንደሆነ አምናለሁ እናም ድምጽህን መስማት እፈልጋለሁ፡፡ ደህና እሆን ዘንድ በአላማ አዳምጥህና አድርግ ያልከኝን አደርጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon