እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። አሁንም ስንፍና አድርገሃል። ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ሰልፍ ይሆንብሃል። – 2 ዜና 16፡9
እግዚአብሔር እርሱ ስለሚወደው ጉዳይ የሚወዱ ሰዎችን እየፈለገ ነዉ፡፡ እርሱን በሙሉ ልባቸዉ የሚፈልጉትን እየፈለገ ነዉ፡፡ አብረዋቸዉ የሚሰሩ ሰዎችን፣ ጎረቤቶቻቸዉን፣ በጉዳት ዉስጥ ያሉትን ድሆችንና ጠፍተው ያሉን ሰዎች የሚወዱ ሰዎችን እየፈለገ ነዉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንድናደርገዉ ያዘዘንን ማድረግ ለመጀመር ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን እየፈለገ ነዉ፡፡
2 ዜና 16፡9 የሚነግረን እግዚአብሔር ራሱን ሊገልጥላቸዉ ልባቸዉ ንጹህ የሆኑ ሰዎችን እየፈለገ እንደሆነ ነዉ፡፡
ከእነዚያ ሰዎች አንዱ ነህን? ካልሆንክ እኔ የማበረታታህ እንደነዚያ ዓይነት እግዚአብሔር የሚፈልገዉ ሰዉ መሆን እንደምትችል ነዉ፡፡
ለረጅም ዘመን በቤቱ የኖርክም ሁን ገና መጀመርህም ይሁን እግዚአብሔርን በፍቅር የሚፈልገውና መንፈስ ቅዱስን የሚሰማ ሰዉ መሆን ትችላለህ፡፡ በተጎዱ ሰዎች ህይወት ልዩነት የምታመጣ ንቁ ሰዉ መሆን ትችላለህ፡፡
ዛሬ! ተነሳ እግዚአብሔር የሚፈልገዉ ሰዉ ሁን፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ! ከማንኛዉ ነገር በላይ አንተ የምትፈልገዉ ዓይነት ሰዉ መሆን እፈልጋለሁ፡፡ እንድሄድ ወደምትፈልገዉ ቦታ ምራኝ፡፡ ሌሎች ሰዎችን የምወድ፣ ቃልህን የምታዘዝና አንተን በእዉነት የማዉቅ ሰዉ አድርገኝ፡፡