እግዚአብሔር ከባዱን መከራህን ለመልካም መጠቀም ይችላል

እግዚአብሔር ከባዱን መከራህን ለመልካም መጠቀም ይችላል

እናንተ ክፉ ነገርን አሰባችሁብኝ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ ለመልካም አሰበው። – ዘፍ 50፡20

እግዚአብሔር ከጥቂት ጊዜ በፊት እንዲህ ተናገረኝ “ጆይስ እስከአፍንጫሽ ጫፍ ወይም መጨረሻ (ብዙም ሩቅ አይደለም) ተመልክተሽ ጥሩ የማይመስል ነገር ጥሩ አይደለም ብለሽ ታስቢያለሽ ፤ ነገር ግን እኔ ከጅማሬዉ እስከፍጻሜ አያለሁ ምክንያቱም እኔ ጅማሬም ፍጻሜም ነኝና ደግሞም አንቺ ማታዉቂያቸዉን ብዙ ነገሮች አዉቃለሁ፡፡”

እኛ በከፊል እናዉቃለን ነገር ግን እግዚአብሔር ሁሉን ያዉቃል፡፡

በዘፍ 50፡20 ላይ ዮሴፍ እጅግ ክፉ ላደረጉበት ወንድሞቹ እየተናገረ ነዉ፡፡ እነርሱ ወደ ጉድጓድ ሲጥሉትና ለባርነት ሲሸጡት እየጎዱት እንደሆነ ያስቡ ነበር እግዚአብሔር ግን እነዚያን መከራቸዎች ተጠቅሞ ዮሴፍን ትልቅ ተጽዕኖ ወደ ሚያመጣበት ቦታ የማድረስ ዕቅድ ነበረዉ፡፡

አንዳንድ ጊዜ አሰቃቂ ናቸዉ ብለን የምናስባቸዉ ነገሮች ወደ ትልቅ በረከት ያዞሩናል፡፡ ትልቁ መከራህ ትልቅ እምነት ያሳድግልሃል፡፡ ጉድጓዱ ወለል ላይ ትሆን ይሆናል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በአንተ ህይወት ወዳለዉ ጥሪ ሊመራህ ያንን ጉድጓድ መስፈንጠሪያህ አድርጎ የመጠቀም ዕቅድ አለዉ፡፡ አስታዉስ እግዚአብሔር ሁሉን ማየት ይችላል ደግሞም እነዚያን መከራዎች ለመልካም ነገር ይጠቀምባቸዋል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ! እኔ የአፍንጫዬን ጫፍ እንኳ ማየት አልችልም ግን አንተን አምነሃለሁ ምክንያቱም ሁሉን እንደምታይ አዉቃለሁና፡፡ ከመከራዎች መልካምን ነገር እንደምታወጣ አምናለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon