እግዚአብሔር ወደ ህይወት ይመራሃል

እግዚአብሔር ወደ ህይወት ይመራሃል

« …በፊታችሁ ሕይወትንና ሞትን በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ፤ እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ፤»(ዘዳ.30፡19)።

በዮሐ.16፡8 ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስ ዓለምን ስለኃጢአትና ስለጽድቅ «እንደሚወቅስና እንደሚያሳምን» ተናገረ። መንፈስ ቅዱስ እንደሚኮንን ምንም የተናገረው ነገር የለም። እርሱ ያለው እርሱ «ስለ ኃጢአትና ስለ ጽድቅ እንደሚወቅስ ወደ መታየት እንደሚያያመጣ ነው።

መንፈስ ቅዱስ የኃጢአትን ውጤትና የጽድቅን ዉጤት በመግለት ሰዎች የሚጓዙበትን መንገድ እንዲያስተውሉ ያደርጋል። እርሱ ሰዎች ህይወትን መምረጥ እንዲችሉ እርሱን እግዚአብሔርን ይጠይቁ ዘንድ በመልካምና በክፋት መካከል ያለውን ልዩነት፤ በበረከትና በመርገም መካከል ያለውን ልዩነት፤ በህወትና በሞት መካከል ያለውን ልዩነት በትክክል ያሳያል።

ሰዎች በኃጢአት ሲኖሩ የሚኖሩት ህይወት የምስኪንና የርግማና ችግር ያለበትን ህይወት ይኖራሉ። እኔ ከዓመታት በፊት የነበረውን ስለማውቅና አንድም የተረጋጋ ጊዜ ስላልነበር ሥራዬ ብዬ ወደ ሰዎች እሮጣለሁ። ከእነዚህ መካከል አንዳንዶቻቸው ለእግዚአብሔር የሚኖሩ አልነበሩምና ህይወታቸው የተበላሸ (ሻካራ)፣ አባጣጎርባጣ የህይወት ሥርዓት ያላቸው በላያቸው ላይ ጉዳት ለማድረስ የመረጡበት ነበር። መራራ፣ ሀዘን፣ መከራ ያለበት ምርጫ እንደመረጡ የሚታይ ነው ምክንያቱም ኃጢአት ሀዘንተኛና ያለእድሜያቸው ያረጁ ሆነው እንዲታዩ አድርጎ እንዳስቀራቸው ይታያል። እነርሱ ደስተኞች አይደሉም፣ አሉታዊ ህይወት የሚመሩ፣ ምንም እርካታ የሌላቸው ግለሰቦች ብዙውን ጊዜ በመራርነት የተሞሉ ናቸው። ምክንያቱም ህይወታቸው አንድም ጊዜ መልካም ሆኖ ስለማያውቅ ነው። በቀጥታ ህይወታቸው እነርሱ የመረጡት የክፉ ምርጫ ውጤት እንደሆነ ማረጋጋጥ አልቻሉም።

የኃጢአት ውጤት ምናልባት በሁሉም ሥፍራ ይታይ ይሆናል። እግዚአብሔርን በሚወዱትና በሚያገለግሉትና በሌሎቹ እግዚአብሔርን በማይወዱትና በማያገለግሉት መካከል ትልቅ ልዩነት መኖሩ ግልጥ ነው። እግዚአብሔር ትክክለኛውን ምርጫ አንድንመርጥ ይመክረናል፣ እርሱም ለእኛ ደስታ ይሆን ዘንድ የሚፈልገውን ወደ ህይወት የሚመራንን እንድንመርጥ ይፈልጋል። በእያንዳንዳችን ፊት ሁለት ዓይነት መንገዶች አሉ። ሰፊው መንገድ ወደ ኃጢአትና ወደ ጥፋት የሚመራንና ቀጭን መንገድ ወደ ህይወት የሚመራን (ማቴ.7፡13-14)። ዛሬና ለሁልጊዜው እኔ የማበረታታህ ህይወትን እነድትመርጥ ነው።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ ትክክለኛ ምርጫ ትክክለኛ ህይወት ይሆናል።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon