እግዚአብሔር የሚያስፈልግህን ያውቃል

እግዚአብሔር የሚያስፈልግህን ያውቃል

« …እናንተ በተስፋ የምትኖሩ እስሮች ሆይ፥ ወደ ጽኑ አምባ ተመለሱ፤ ሁለት እጥፍ አድርጌ እንድመልስልሽ ዛሬ እነግርሻለሁ» (ዘካ. 9፡12)።

አንድ ቀን አንድ ስሜቴን የጎዳ ነገር ተከስቶ ነበር። ዴቭና እኔ በተፈጠረው ሁኔታ ውስጥ ትክክል ባልሆነ ወይም ፍትሀዊ ባልሆነ መንገድ አስተናግደውን ነበር፣ እናም ስለጉዳዩ በጣም በስሜት ተጎዳሁ። እኔ በአውሮፕላን ማረፊያ ነበርኩ፣ እናም መጽሐፍ ቅዱስ ለማንበብ ወሰንኩ። ከዚያም ለዛሬ የተመረጠውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ዘካ. 9፡12 ከፍቼ አነበብኩና ቃላቱ ከገጽ ወደ እኔ የዘለለ ነው የመሰለኝ።

ይህንን ጥቅስ ባየሁት ጊዜ፣ እምነቴ ወደ አዲስ ደረጃ ከፍ አለ። ስላለሁበት ሁኔታ እግዚአብሔር እየተናገረኝ እንዳለ ያለምንም ጥርጣሬ አውቀው ነበር። ተስፋ የማልቆርጥ መሆኔንአውቅ ነበር፣ እኔ ትክክለኛውን አመለካከት ቢኖረኝእግዚአብሔር በሁኔታው ውስጥ የተወሰደብኝን ነገር እጥፍ አድርጎ በቀኑ ውስጥ እንደሚሰጠኝ እንደማይ ተስፋ አደርጋለሁ።ከአንድ ዓመት ያህል በኋላ በቀኑ እግዚአብሔር እስደናቂ ነገር አደረጋና ያለፍትሃዊነት ተወስዶብኝ የነበረውን እንደተስፋ ቃሉ እጥፍ አድርጎ እንደሚያድስ ያረጋገጠልኝና እርሱ በአላግባብ የጎዱኝ ጋር ያለውን ግንኙነት አደሰው።

መንፈስ ቅዱስ በትክክል ስለሚያስፈልግህን ያውቃል። መጽሐፍ ቅዱሴን ከፍቼ ስላለሁበት ሁኔታ እንዲናገረኝና እንዲረዳኝ ተስፋ አድርጌ እጠብቅ ነበር፣ ነገር ግን እርሱ እኔን ለማጽናናት ብቻ ሳይሆን ከትልቁ ተስፋዬ በበለጠ ያጣሁትን አደሰልኝ። ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍልና ሌሎችም ክፍሎች የአንተ የተስፋ ቃሎች ጭምር ናቸውና እግዚአብሔር በእነርሱ ለአንተ እየተናገረ ነው።በማንኛውም ጊዜ መጽናናትንና ምሪት የምትፈልግ ስትፈልግ ወደ እግዚአብሔር ቃል እንድትሄድ አበረታታሃለሁ። ይህ በእውነት በሁሉም የህይወት ሁኔታዎች ውስጥ እኛ የምንፍልገውን መልስ በእርሱ የተካተተ ነው።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ እግዚአብሔር ላለህበት መከራ እጥፍ መልስ ይሰጥሃል (እርሱ ለቀደመው መከራህ እጥፍ በረከትን ይሰጥሃል)።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon