እግዚአብሔር የሰጣችሁ ህልም እውን ሲሆን መመልከቻው መንገድ

እግዚአብሔር የሰጣችሁ ህልም እውን ሲሆን መመልከቻው መንገድ

አንተ ታካች፤ወደ ጉንዳን ሂድ፤ዘዴውን አስተውለህ ጠቢብ ሁን፤አዛዥ የለውም አለቃም ሆነ ገዥ የለውም፤ሆኖም ግ በበጋ ምግቡን ያከማቻል፤በመከርም ወቅት ቀለቡን ይሰበስባል፡፡ – ምሳ 6፡6-8

እግዚአብሔር ልጆቹ ይከተሉት ዘንድ ትልቅን ህልም ሰጥቷቸዋል፡፡ እነዚያ ህልሞች እንዲፈጸሙ ራስን በማሳደግ ሂደት ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር በመተባበር የስልጠና ጊዜን ማሳለፍ አለብን፡፡ ይሄ ሂደት ጊዜን ፣ ቁርጠኝነትን እና ጠንካራ ስራን ይፈልጋል፡፡

አሁን አሁን ከምቾት ጋር በጣም ተላምደናል፡፡ እቃ ለማጠብ እና ልብሳችንን አጥቦ ለማድረቅ ማሽኖችን መጠቀም ጀምረናል፡፡ አንድን ቁልፍ ተጭነን ብቻ ማሽኑን ስራ እናስጀምረዋለን፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ እንደዛ የሚሰራ ምንም ነገር የለም፡፡ እቅዶቹን እና አላማውን አስፈላጊውን ክህሎት ሳታዳብሩ ማሟላት አትችሉም፡፡

በምሳሌ መጽሀፍ ላይ ስለ ጉንዳን እናነባለን፡፡ ጉንዳኖች በትንሽ ቁርጠኝነት ከመጠናቸው በላይ ይሰራሉ፡፡ በጣም የተነቃቃን እና ራሳችንን የምንገዛ መሆን እንዳለብን ከእነርሱ ትልቅ ትምህርት መማር እንችላለን፡፡

ለክርስቶስ ለመኖር እንደዚህ ያለ በራስ የመነቃቃት እና ራስን የመግዛትን ነገር ስታዳብሩ እግዚአብሔር እንድትሆኑ የፈጠራችሁን ሁሉ መሆን ትጀምሩና እንደውም ሌሎችን በዚህ ሂደት ውስጥ ለእርሱ ትመራላችሁ፡፡ ስለዚህ በቁርጠኝነት በማደግ እና ህልሞቻችሁ እውን ሲሆኑ በማየት ቀጥሉ!


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ አንተ ስትፈጥረኝ እንድሆን የፈለግከውን ሁሉ መሆን እና በልቤ ያስቀመጥከውን ህልም መፈጸም እፈልጋለሁ፡፡ በአንተ ላይ አተኩሬ እንድቀጥል፣በክርስቶስ ለማደግ የሚያስፈልገውን ጊዜ ፣ ቁርጠኝነት እና ጠንካራ ስራ ሰጥቼ ለእኔ ያለህን እቅድ እንድኖር እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon