
ጉልበቴ ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው፡፡ መድኃኒቴም ሆነልኝ፣ ይህ አምላኬ ነው አመሰግነዋለሁ፣ የአባቴ አምላክ ነው ከፍ ከፍም አደርገዋለሁ፡፡ ዘፀ. 15 2
እንደሙሴና እንደ እስራኤል ሕዝብ በዛሬው የጥቅስ ክፍላችን እንደምናነበው እንደ እነርሱ መሆን ይኖርብናል፡፡ እኔ ማሳየት (የማተኩረው) እግዚአብሔር ብርታትን ብቻ አይደለም የሰጣቸው፡፡ (ልክ በብሉይ ኪዳን መጽሐፍት እንደምናነበው) ነገር ግን እርሱ እራሱ የእነርሱ ብርታት ነበር፡፡ በ1ሣሙ 15 29 እግዚአብሔርን እንደ ኃይሉ የሚያዩበት ጊዜያት አሉ፡፡ ነገር ግን ወዲያው ደግሞ ይረሳሉ፡፡
ይህንን በጣም ጠቃሚ እውነት ሲረሱ ሁልጊዜ እንደ ሕዝብ ይስቱና በመውደቅ ሕይወታቸው መጥፋት ይጀምራል፡፡ የኃይላቸው ምንጭ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ሲመለሱ ነገሮች ሁሉ በዙሪያቸው ይስተካከላል፡፡
እግዚአብሔር ኃይልህ እንደሆነ ብታውቅም በእምነት ወደ ሕይወትህ መቀበል ይኖርብሃል፡፡ እኔ ቀኑን ሁሉ የሚጀመረው ያለ እርሱ ብቻዬን ምንም ነገር ማድረግ እንደማልችልና ሁሉን እንዲያስችለኝና ኃይል እንዲሰጠኝ ሙሉ በሙሉ በእርሱ ላይ እደገፋለሁ፡፡ እርሱ እኛን የሚያበረታታው የማያበረታታ ቃሉን በመናገርና ሲያስፈልግ አቅጣጫ በመስጠት ነው፡፡ እርሱ የጥበብ ቃልን ከመናገርና መገለጥ በመስጠት ያበረታናል፡፡ በአካልም ደግሞ መለኮታዊ ኃይል በመስጠት ስንደክምና ስንዝል ያበረታናል፣ አስቸጋሪ ሰዎችንና ሁኔታዎችን መቋቋም እንድንችል ኃይል ይሰጠናል፡፡
በራስህ ከነገሮች ጋር ከመታገል እግዚአብሔር ብርታት እንዲሆንህ ታመነው፡፡ ምናልባት በአንተ ላይ የሚደገፍና አንተ ብቻ የምትደግፋቸውን ሰዎች መረዳት የምትችለው በእግዚአብሔር ላይ የተደገፍከውን ያህል ነው፡፡ ዛሬ የአንተ ብርታት እንደሆነ በእምነት ተቀበልና በቀላሉ ነገሮች ሲከናወኑ በማየት ትገረማለህ፡፡
የዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- እግዚአብሔር ብርታትህ እንዲሆንልህ ፍቀድለት፡፡