እግዚአብሔር የተሰበሩ ማሰሮዎችን ሊጠቀምባቸው ይችላል

እግዚአብሔር የተሰበሩ ማሰሮዎችን ሊጠቀምባቸው ይችላል

አሁን ግን፥ አቤቱ፥ አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን አንተም ሠሪያችን ነህ፥ እኛም ሁላችን የእጅህ ሥራ ነን። – ኢሳ 64፡8

እግዚአብሔር ፍጹም እንድንሆን አይጠብቅም፡፡ የሰራን እርሱ ስለሆነ ሰዎች መሆናችንንና ስህተትን ልንሰራ እንደምንችል ያውቃል፡፡የእኛ ስራ በየዕለቱ ተነስተን እርሱ በሰጠን ጸጋ እርሱን ለማገልገል የተቻለንን ሁሉ ማድረግ ነው፡፡ ስህተትን ስናደርግ ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር ማስተካከል ያለብንን ነገር በማስተካከል ይቅርታውን በመቀበል ወደ ፊት መቀጠል አለብን፡፡

በርካታ ሰዎች ፍጹም ባለመሆናቸው ምክንያት እግዚአብሔር ሊጠቀምባቸው እንደማይችል ይሰማቸዋል፡፡ ነገርግን ይህ ውሸት ነው፡፡ ሸክላ ሰሪው እግዚአብሔር የተሰበሩ ማሰሮዎችን (እኛን ማለት ነው) ለስራው ይጠቀማል፡፡ ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን የእግዚአብሔር በጎነትና ብርሃን መያዣ ዕቃዎቹ ነን፡፡ ይህንንም በጎነቱንና ብርሃኑን ተሸክመን ወደ ጨለማው ዓለም ተሸክመን በሄድንበት ሁሉ ለሰዎች የምናካፍል ነን፡፡

ጉድለቶቻችሁን አትፍሩ፣ ይልቁንም እውቅና በመስጠት እግዚአብሔር እንዲጠቀምባችሁ ፍቀዱለት፡፡ ባልሆንከው ነገር መጨነቅን አቁምና የሆንከውን ማንነትህን ለእግዚአብሔር ስጥ፡፡ ትኩረትህን ፍጹም በሆነው እግዚአብሔር ላይ አድርግ፡፡ በአንተና በውስጥህ ሊሰራ በሚችለው ነገር ላይ ይሁን፡፡ የተሰበረ ማሰሮ ብትሆንም ሌሎችን ደስተኛ ማድረግ ትችላለህ፡፡ በዙሪያህ ያሉትን ሰዎች ማበረታታት፣ ማነጽ እና መምከር ትችላለህ፡፡ ችሎታህንና ጸጋህን እግዚአብሔርን ለማገልገል ተጠቀምበት፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ የተሰበረ ማሰሮ ሆኜ ሊሆን ይችላል ነገር ግን አንተ ሸክላ ሰሪ ነህ፡፡ ከጉድለቶቼ ጋር ለዓላማህ ልትጠቀምብኝ ትችላለህ፡፡ በዙሪያየ ወዳሉት እንዳደርስ በራስህ በጎነትና ብርህን ሙላኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon