እግዚአብሔር የገባልንን ቃል ኪዳን እናሳስበዉ

ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ጕበኞችን በቅጥርሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ ቀንና ሌሊት ከቶ ዝም አይሉም፤ እናንተ እግዚአብሔርን የምታሳስቡ፥ ኢየሩሳሌምን እስኪያጸና በምድርም ላይ ምስጋና እስኪያደርጋት ድረስ አትረፉ ለእርሱም ዕረፍት አትስጡ። (ኢሳ 62፡6)

የዛሬዉ ቃል እግዚአብሔር የገባልንን ቃል ኪዳን እንድናሳስበዉ የሚናገረን ሲሆን ይህንንም ለማድረግ የተሻለዉ መንገድ ደግሞ ቃል የገባልንን ቃል ራሱ በመፀለይ ነዉ፡፡

እግዚአብሔር ለቃሉ በጣም ትልቅ ዋጋ ይሰጣል፤ ለኛም እንደዚሁ መሆን አለበት፡፡ እሱ ሲጀመር የሚናገረን በቃሉ ሲሆን ድምፁንም በእምነት መስማት ከኛ ይጠበቃል፡፡. ብእርግጥም በአዲሱ መደበኛ ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ በመዝሙር 138:2 ላይ፡- “ወደቅዱስመቅደስህእሰግዳለሁ፤ ስለምሕረትህናስለእውነትህስምህንምአመሰግናለሁ፥በሁሉላይቅዱስስምህንከፍከፍአድርገሃልና።” ይህ ቃል የሚነግረን እግዚአብሔር ቃሉን ከስሙ በላይ እንደሚያጎላ ነዉ! እሱ ቃሉን እንደዚህ የሚያከብረዉ ከሆነ፤ እኛም ቃሉን ለማወቅ ቅድምያ መስጠት፤ ቃሉን ማጥናት፤ ቃሉን መዉደድ፤ ቃሉ በህይወታችን ስር እንዲሰድ ማድረግ፤ ቃሉን ከምንም በላይ ማክበር፤ ቃሉን በፀሎታችን ዉስጥ ማካተት ይኖርብናል፡፡

ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ቃሉን አክብረን ራሳችንን ለእሱ አሳልፈን ስንሰጥ፤ ለቃሉ መታዘዛችንን ያሳያል (ዮሐ 15:7 ተመልከቱ) ፡፡ በቃሉ ዉስጥ መኖርና ቃሉ በኛ ዉስጥ እንዲኖር መፍቀድ በፀሎት ላይ ያለንን አቋም ከማጠናከርና ፀሎታችንም መልስ እንዲያገኝ ከማድረግ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነዉ፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ስንፀልይ የእግዚአብሔር ፍቃድ ለሌለበት ነገር ቦታአለመስጠታችንን ያሳያል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ህያዉ ቃል ነዉ (ዮሐ 1:1-4 ን ተመልከቱ) በቃሉ ወስጥ ስንኖርፀሎቶቻችን የሚያስደነቅ ጉልበት ይኖራቸዋል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ የእግዚአብሔር ቃል አእምሯችሁን ያድሳል እግዚአብሔር እንደሚያስበዉ ሃሳብ እንድታስቡም ያስተምራችኋል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon