
የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈሩ እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ፣ እግዚአብሔርም አደመጠ ሰማም እግዚአብሔርም ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ መጽሐፍ በሬቱ ተፃፈ፡፡ ሚክ 3 16
የዛሬው ጥቅስ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ንግግርን እኛም የእርሱን በጎነት ስንናገር ይወዳል የምል ነው፡፡ እግዚአብሔርም ይህንን ንግግራችንን ስሰማ የማስታወሻ መፃፊያውን ያወጣና ይመዘግብበታል፡፡ እርሱ የእኛን ማጉረምረም፣ ብስጭት፣ ምሬት፣ በማስታወሻው አይዝም፡፡ ነገር ግን እርሱ የሚመዘግበው እኛ እርሱን ስናመሰግን የምንናገረውን የምሥጋና ቃላት የከንፈሮቻችን ፍሬዎችን ነው፡፡
ሚስትህ ልጆችህ እንዲህ ሲነጋገሩ ስትሰማ ምን እንደሚሰማ አስብ፣ ልጆችህ እናታችንና አባታችን በጣም የተከበሩ ናቸው፡፡ በዓለም ላይ በጣም ምርት እናት አላችን ለማመን የሚያስቸግር ምርጥ እናትና አባት አሉን አይደለም; እነርሱ በአካባቢያችን ካሉት በጣም ጥሩዎች ናቸው፡፡ ከልጆችህ አንደበት እንዲህ አይነት ምስክርነት ስትሰማ ፈጥነህ ሳትዘገይ ትባርካቸዋለህ፡፡ ደግሞም ላለመባረክ አያስችልህም፡፡
ነገር ግን በሌላ መንገድ ወደ ቤት እየገባህ እያለህ የአንተ ልጆች እኔ በጣም ያመኛል ደግሞ ከብዶኛል አባቴና እናቴ ለእኛ ምንም አያደርጉም፡፡ እነርሱ ለቤቱ ያወጡትን ደንብ ብቻ ላይ ያተኩራሉ፡፡ ለእኛ ፈታ ብን ደስተኞች እንድንሆን እያመቻቹም እናታችን ሁልጊዜ የቤት ሥራችንን እንድንሰራ ነው የምትጨቃጨቀን በእርግጥ ወላጆቻችን የሚወዱን ከሆነ እኛ የምንፈልገውን ያደርጉልን ነበር ሁሉም ሃሣባቸው ጥሩ አይደምን;
ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ሕይወት ከላይ ከገለጸኩት ሁለቱ ሃሣቦች (ገለፃዎች) የተለየ አይደለም፡፡ እኛ የእግዚብሔር ልጆች ነን! እኛ የምንናገረውን ነገር ሁሉ ይሰማናል፡፡ እንዲሁም ገና በልባችን ያለውን ያልተናገርነውን ያውቃል፡፡ ስለምን አይነት ነገር ስንናገር ልሰማን ይፈልጋል!እርሱ እንዴት የላቀ ነዉ!እንዴት የከበረ ነዉ! በጣም ግሩም ስራ ሰርቶዋል! እግዚአብሒርን መለካምነት ከልብን ተናገርና በዚያን ጊዜ ለእግዚአብርን ምቹ ሁኔታ ትፈጥራለህ፡፡
ዛሬ የእግዚአብሒርን ቃል ለአንተ፡- የእግዚአብሒርን ንግግር ለመስማት ደስ የሚያሰኘ ከአፍህ ብቻ ሳሆን ከልብህ ተናገር፡፡