እግዚአብሔር ፈጽሞ አይለወጥም አንተ ግን ልትለወጥ ትችላለህ

እግዚአብሔር ፈጽሞ አይለወጥም አንተ ግን ልትለወጥ ትችላለህ

እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ ስለዚህ የጠፋችሁ አይደላችሁም። – ት.ሚልክያስ 3፡6

ለምንድነዉ ምንም አይለወጥም… እንድህ እንደሆንኩ እቀጥላለሁ…. ሁኔታዎች ፈጽሞ አይለወጡም…. እርሱ ፈጽሞ አይለወጥም….እርሷ ፈጽሞ አትለወጥም…. እንደ እንትና እና እንትና ፈጽሞ መልካም መሆን አልችልም…. ብለን ስናስብ ራሳችንን የምናገኘዉ?

ፈጽሞ የማይለወጠዉ ብቸኛዉ ነገር እግዚአብሔር ብቻ ነዉ፡፡ ሁሉም ነገር ሊለወጥ ይችላል፡፡

ነገር ግን በሁኔታህ ለዉጥ የማየት ተስፋ ከሌለህ እርግጥ ለዉጥ ላይመጣ ይችላል፡፡ እኛ መቆጣጠር የማንችላቸዉን ሁኔታዎች ብንተዉና ተስፋችንን በእግዚአብሔር ላይ ብናደርግ ኖሮ መሰቃየት የሌለብንን ብዙ ነገር ባለለፍን ነበር፡፡

መልካሙ ዜና ይኸዉና፡ ከወሰንክ ህይወትን ማጣጣም ትችላለህ፡፡ ነገር ግን ዘላቂ ደስታ ማጣጣምህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነ ግን እርግጠኛ መሆን በእዉነት ማመን አለብህ፡፡ ከዚያ ወደዚያ ደስታ ለመግባት መወሰን አለብህ ይህም ለአካላዊ፣ ለአእምሮአዊ፣ ለስሜታዊና መንፈሳዊ ጤንነትህ ወሳኝ ነዉ፡፡

እግዚአብሔር አይለወጥም ግን ከፈቀድክለት አንተን ሊለዉጥህ ይችላል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ አንዳንድ ጊዜ ሁኔታዎቼ እንደማይለወጡ ይሰማኛል፤ ነገር ግን ሁኔታዎቼንም እኔንም ልትለዉጥ ትችላለህ፤ ደስታዬን መቀበል ወስኜአለሁ ህይወቴንም እንደምትለዉጥ አምንሃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon