እፍረትን ተወው

እፍረትን ተወው

መጽሐፍ። በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና። – ሮሜ 10፡11

አንድ ሰዉ በሀፍረት ላይ የተመሰረተ ተፈጥሮ ሲኖረዉ ፤ ልክ እኔ እንዳደረኩት ፣ እንደ ድብርት ፣ ብቸኝነት፣ መገለልና ባይተዋርነትን ለመሳሰሉ ዉስጣዊ ችግሮች ምንጭ ወይም ሥር ይሆናል፡፡ ሁሉም ዉስጣዊ ችግሮች መሰረታቸዉ ሀፍረት ነዉ ፤ ዕጽ ፣ አልኮል እና ሌሎችም ሱሶች ፣ ከመጠን ያለፈና የወረደ የመመገብ ፍላጎትን የመሳሰሉ የአበላል መዛባቶች ፣ የገንዘብ ሱስ ቁማር ፣ የወሲብ ችግርና ሁሉም ችግሮች መሰረታቸዉ ሀፍረት ነዉ፡፡

የአንዳንድ ሰዎች ከመጠን በላይ በስራ መጠመድ ከሀፍረት የተነሳ ነዉ፡፡ ህይወትን ማጣጣም የማይችሉ ግን ስራ ወዳድ ሰዎች ብዙ ናቸዉ ፤ ቀንና ማታ ካልሰሩ ሃላፊነት የማይሳማቸው፡፡ እርግጥ አንዳንድ ሰዎች እንደ እኔ ናቸዉ በራሳቸዉ ፈታ ካሉ ጥፈተኝነት የሚሰማቸዉ፡፡

ምንአልባት በበዛ የስራ ፍቅር እየታገልክ ይሆናል፣ ምን አልባትም ሀፍረት ተኮር የሆኑ ብዙ ትግሎች ይኖሩብህ ይሆናል፡፡ ነጥቡ  ሀፍረት ሊያከስረን ይችላል የሚል ነዉ፡፡ ልንፈቅድለት ግን አይገባም። እምነታችንን በእግዚአብሄር ስናደርግና ህይዎታችንን ስንሰጠው ሃጢያታችንን ያስወግድልናል። ኢየሱስ እኛን ከሃጥያት በማንጻትና ጥፋታችንን በመሸፈን በእግዚአብሄር ህልውና ውስጥ እኛ ልጆቹ መኖር እንችል ዘንድ ሞቷል።

ሃፍረት እያጠቃችሁ ከሆነ ይህንን እውነታ ለማስታዎስ ሰአቱ አሁን ነው ፡- እግዚአብሄር ይወዳችኋል። ይህንን በማመን እርሱ ላይ በምትደገፉ ግዜ ሃጢያታችሁን ያስወግዳል።


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ አንተን ካመንኩ በሀፍረት መኖር እንደሌለብኝ አዉቃለሁ፡፡ በአንተ መገኘት በነጻነት እንድኖር ሀፍረቴን ስለወሰድከዉ አመሰግንሃለሁ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon