ከሁሉም ጋር በሰላም ኑሩ

ከሁሉም ጋር በሰላም ኑሩ

ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ። – ሮሜ 12፡18

እኔ የተማርኩት ጠቃሚ ነገር “እንዳልሰበር መጠምዘዝን” ነዉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሚለዉ ራሳችንን (ለሰዎች፣ ለነገሮች) እንድናስተካክል ነዉ እናም በተቻለ መጠን ከሰዉ ሁሉ ጋር በሰላም ኑር፡፡ (ሮሜ 12፡16 18)

የእግዚአብሔርን ቃል በሕይወቴ ቀዳሚ ከማድረጌና የመታዘዝ ህይወት ለመኖር ከመወሰኔ በፊት የራሴ መንገዶች ነበሩኝ፡፡ ለማዳ አልነበርኩም፤ የፈለግሁት ሰዉ ሁሉ ለእኔ ምቹ እንዲሆን ነበር የምፈልገው፡፡ እርግየጥ ያ ብዙ ጠብና ጭንቀት አምጥቷል፡፡

አሁን መለስለስን ተምሬአለሁ፡፡ ተስፋ መቁረጥና ነገሮችን እንደ ዕቅዴ አለመስራት ቀላል አይደለም ግን ከመበሳጨት እና ከመታወክ ይሻላል፡፡

በግንኙነቶችህ ውስጥ ሰላም እንዲኖርህ የምትፈልግ ከሆነ ተለዋዋጭ ለመሆን [ግትር ላለመሆን] ፍቀድ፡፡ ወደ ራስህ መንገድ ብቻ መግፋት በዙሪያህ ያሉትን ይጎዳል ያበሳጫልም፡፡ ነገር ግን ከሰዉ ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ የሚለዉን የጳዉሎስን ማበረታቻ ስትቀበል፤ መንፈስ ቅዱስ ግንኙነቶችህን በሰላሙና በደስታዉ ይሞላል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ! እንዳልሰበር ግትር እንዳልሆን እርዳኝ፤ በግንኙነቶቼ ሰላምህን ስለምፈልግ ግትር ላለመሆን መርጬአለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon