ከመቼውም ጊዜ በላይ የተሻለ የሚሆንልህ ወዳጅ

ከመቼውም ጊዜ በላይ የተሻለ የሚሆንልህ ወዳጅ

ከወንድም ይልቅ የሚቀርብ ወዳጅ አለ። (ምሳሌ 18 24)

ለውጤታማ ጸሎት እና ከእግዚአብሔር ጋር ላለ የጠበቀ ግንኙነት በጣም አስፈላጊ የሆነውን ቁልፍ ነገር መለየት ካለብኝ እግዚአብሔርን እንደ ወዳጅ መቅረብ ነው እላለሁ። እርሱ እንደ ወዳጆቹ እንደሚያየን በማመን ወደ እግዚአብሔር ስንቀርብ አዳዲስ ድንቆች ይሆኑልናል። ነፃነትን እና ድፍረትንም እንለማመዳለን እነዚህ ደግሞ ለውጤታማ ፀሎት የሚረዱ ናቸው።

እግዚአብሔርን እንደ ወዳጅ የማናውቀው ከሆነ እና እሱ እኛን እንደ ወዳጆቹ አድርጎ እንደሚመለከተን እርግጠኞች ካልሆንን እኛ የምንፈልገውን ለመንገርም ሆነ ማንኛውንም ነገር ለመጠየቅ ወደኋላ እንላለን። ከእግዚአብሔር ጋር ጠንካራ እና የቆየ ግንኙነት ካለን ጸሎታችን አግባብነት ሊኖረው ይችላል፤ ነገር ግን ለእርሱ ያለንን አክብሮትና ፍርሃት ሳናጣ፣እንደ ወዳጃችን ወደ እርሱ ከሄድን፣ ከእሱ ጋር ያለን ተግባቦት ትኩስ፣ አስደሳች እና የጠበቀ ይሆናል።

ተፈጥሯዊ ወዳጅነት መውደድን እና መወደድን ያካትታል። ይህ ማለት ሊረዳህ፣ ሊያበረታታህ እና ሁል ጊዜም የአንተን ጥቅም ለማስጠብቅ የሚችል አንድ ሰው ከጎንህ እንዳለ ማወቅ ማለት ነው። ወዳጅ ማለት ከፍ ያለ ስፍራ የምትሰጠው፣ ባልደረባህ፣ አጋርህ፣ ለአንተ ተወዳጅ የሆነ ሰው፣ አብረኸው ጊዜ ለማሳለፍ የምትፈልገው እና የምትደሰትበት ሰው ነው። የሆነ ሰው ወዳጅ የምትሆነው ጊዜህን በእርሱ ላይ ወይም ከእርሱ ጋር በማጥፋት እና ሕይወትህን በማካፈል ነው። እግዚአብሔርን እንደ ወዳጅህ እንድትመለከት አበረታታሃለሁ። በአክብሮት እና በክብር ያዘው፣ ነገር ግን ከምድራዊ ወዳጅህ ጋር እንደምታደርገው ሁሉ በግልፅ እና በቀላሉ ከእሱ ጋር መግባባትን ተማር። እርሱ ሊኖርህ ከሚችል ከየትኛውም ወዳጅ በላይ ነው።

ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ የእግዚአብሔር ወዳጅ ነህ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon