ከራስ ጋር ያለ ግንኙነት

ከራስ ጋር ያለ ግንኙነት

መተላለፍህን፦ ስለ እኔ ስል የምደመስስ እኔ ነኝ ኃጢአትህንም አላስብም። – ኢሳያስ 43:25

ከራስዎ ጋር ግንኙነት እንዳለዎት ያውቃሉ? ብዙ አስበህበት ላታውቅ ትችል ይሆናል ነገር ግን ብዙ ጊዜህን የምታሳልፈው ከሌሎች ሰዎች ይልቅ ከራስህ ጋር ነው፡፡ ከራስ ጋር ጊዜ ወስዶ ማሳለፍ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም ልትሸሸውና ልታመልጠው የማትችለው አንድ ሰው አንተን ብቻ ስለሆንክ፡፡

ራሳችንን መውደድ አለብን፡፡ ይህ ማለት ግን በራስ ወዳድነትና ራስን ብቻ ማዕከል ባደረገ የኑሮ ዘይቤ መዋጥ ማለት ሳይሆን ሚዛናዊ በሆነና በመሰረታዊነት የእግዚአብሔር ፍጥረት መልካምና ትክክል መሆኑን በሚያረጋግጥ መንፈስ መሆን አለበት፡፡ ማንም ፍጹም የሆነ የለም፡፡ ባለፍንባቸው መጥፎ አጋጣሚዎች ምክንያት የተለያየ ጉድለት ያለብን ሰዎች ልንሆን እንችላለን ፣ ይህ ማለት ግን እኛ ለምንም የማንጠቅም ዋጋ ቢሶች ነን ማለት አይደለም፡፡

ለራሳችን የሚኖር ፍቅር ይህንን ዓይነት መሆን አለበት ፤ እግዚአብሔር እንደሚወደኝ አውቃለሁ ፣ እግዚአብሔር ሊወደው የመረጠውን ይህንን ሰው እኔም ልወደው እችላለሁ ልንል ይገባል፡፡ የምናደርገውን ነገር ሁሉ ላንወደው እንችል ይሆናል ነገር ግን እግዚአብሔር ስለተቀበለኝ እራሴን እቀበላለሁ የሚል እምነት ሊኖረን ይገባል፡፡

ማዳበር ያለብን የፍቅር ዓይነት ‘’እግዚብሔር በየዕለቱ እንደሚለውጠኝ አምናለሁ፡፡ እግዚአብሔር የተቀበለውን እኔነቴን አልቃወም፡፡ ሁልጊዜ ባለሁበት እንደማልቀር ስለማወቅ እራሴን አሁን ባለሁት ሁኔታ እቀበላለሁ፡፡’’ መሆን አለበት።


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚብሔር ሆይ፣ ኢሳያስ 43:25 ላይ እንደተገለጸው፣ ኃጢያቴን ደምስሰህ እኔን ተቀበልከኝ፡፡ ይህ ማለት ራሴን አለመቀበል አልችልም፡፡ አንተ ስለወደድከኝ ጤናማ በሆነ መልኩ እራሴን እንድቀበልና እንድወድ ነጻ ወጥቻለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon