እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው የሚያስደነግጠኝ ማን ነው? – መዝ 27፡1
ሃሳቦችህ በስጋት እንዲዋጡ የምትፈቅድ ከሆነ እግዚአብሔር የሰጠህን ፍጻሜ መድረስ አዳጋች ነዉ፡፡ ስጋት የፍርሃት የቅርብ ዘመድ ነዉ፤ እርሱ በአእምሮህ እንዲቆይ መፍቀድ አንተን ወደ አሳዛኝ ሁኔታ ይመረሃል ደስታህንም ይሰርቃል፡፡
ህንድ ሀገር ላይ ኮንፍረንስ ልናዘጋጅ ስናቅድ ፍርሃትን ተለማምጄአለሁ፡፡ እዚያ ስላለዉ አስደናቂ ዕድል ተደንቄአለሁ ግን ደግሞ በሀገርቱ ስላለዉ የድህነት ሁኔታም ሰግቼአለሁ፡፡ ግን ጌታ ለልቤ ስጋትን እንዳሸንፍና በዚያ ስለሚመጣዉ የቃሉ መገለጥ እንዳተኩር ተናገረኝ፡፡ ከአሉታዊ ነገሮች ጋር እንድነጋገር ራሴን ፈቅጄ ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር እንድለማመደዉ የሰጠኝን የደስታ ስሜት ይወስድብኝ ነበር፡፡
ስጋት ወጥመድ ነዉ ስለዚህ በስጋት እንዳትወድቅ ወስን፡፡ ፍርሃትን የሚያመጡ ወይም ወደ ልብህ ስጋት የሚያመጡ ስለነገ እንደመጨነቅ ያለነገር ሲገጥምህ ወደ መዝሙር 27፡1 ዘወር በልና “እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?” ብለህ ከፍ ባለ ድምጽ ተናገር ጸልይ፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
ጌታ ሆይ! ዛሬ አንተ ብርሃኔና መድሃኒቴ እንደሆንክ አዉጃለሁ፤ ከአንተ የተነሳ በህይወቴ ስለምንም ነገር መስጋት አያስፈልገኝም፤ በአንተ ድል አለኝ፡፡