ከቅሬታ/ቅይማት ጋር መነጋገር

ከቅሬታ/ቅይማት ጋር መነጋገር

እንግዲህ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ዲያብሎስን ተቃወሙት ከእናንተም ይሸሻል፡፡ – ያዕ 4:7

ዙ ክርስቲያኖች ከቅሬታ/ቅይማት ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለባቸዉ ስላልተማሩ በህይወት ተስፋ ቆርጠዉና ተደብረዉ ከመንገድ ጥግ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን ዛሬም ሆነ መቼም በቅሬታ የተሞላ ተስፋ አስቆራጭ ህይወት ትኖሩ ዘንድ የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም፡፡

ከኢየሱስ የምድር አገልግሎት ከፊሉ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ በዲያብሎስ የተጠቁትን ነጻ ማዉጣት ነበር፡፡ ተስፋ የቆረጡ ሰዎች የኢየሱስን ኀይል በተገናኙ ጊዜ ሁሉ አዲስ ተስፋ ያገኙ ነበር፡፡ ያዉ ተመሳሳይ ኀይል ዛሬ ለእኛ ቀርቧል፡፡

በእግዚአብሔር ላይ በማተኮር፣ የተስፋ ቃሎቹን በማሰላሰል፣ ቃሉን በመናገር፣ ራስህንና ያለህበትን ሁኔታ በጸሎት በፊቱ በማስገዛት ቅሬታህን ድል ለመንሳት ይህንን ኀይል ተጠቀም፡፡ ሊረግጥህ የሚፈልገዉን ጠላት በኢየሱስ በኩል ልትዋጋ ትችላለህ፤ ሊያጠፋህ እንዳይችል ተቃወመዉ፡፡

ዲያብሎስ አንድ እርምጃ ወደ አንተ ሲጠጋ፤ አንተም ፊትህን ወደ እግዚአብሔር አዙረህ ጠላት ምን ለማድረግ እየሞከረ እንደሆነ ለመለየት መንፈሳዊ ሐይል ልትቀበል ትችላለህ፡፡ ተቃወመዉ እንዲሸሽህም አድርግ፡፡ ኢየሱስ ካመቻቸልህ ሐይል የተነሳ ጠላትህ ከመሸሽ ዉጪ ሌላ አማራጭ የለዉም፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! ወደ ኋላ የሚጎትቱኝና ተስፋ የሚያስቆርጡኝ ነገሮች ከፊቴ ይመጡ ይሆናል ግን ተስፋ እንደቆረጥኩ አልቆይም፡፡ ወደ አንተ ስቀርብ ዲያብሎስን እቃወማለሁ እርሱም ይሸሻል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon