ከበረከቶቹ በላይ እግዚአብሔርን መፈለግ

ራሳችሁን ከፍቅረ ንዋይ ጠብቁ፤ባላችሁ ነገር ረክታችሁ ኑሩ፤ምክንያቱም እግዚአብሔር፣”ከቶ አልተውህም፤በፍጹም አልጥልህም “ብሎአል፡፡ – ዕብራ 13፡5

“በማንም አልቀናም፣ወይም ሌሎች ባላቸው ነገር አልመቀኝም እግዚአብሔር ከሰጣቸው እንዲደሰቱ ነው የምፈልገው”ማለት የምንችል በእውነት ስንቶቻችን ነን?

ቃሉ ሲናገር ራሳችሁን ከፍቅረ ንዋይ ጠብቁ፤ባላችሁ ነገር ረክታችሁ ኑሩ…(ዕብራ.13፡5)፡፡እግዚአብሔር በዚህ ቃል ላይ የምንኖር መሆናችንን ለማየት ይፈትነናል ብዬ አምናለሁ፡፡

እኛ ምን አይነት ምላሽ እንደምንሰጥ ለማየት- አንዳንዴ የምንፈልገውን ነገር ሁሉ ያለው ሰው ከፊታችን ያስቀምጣል፡፡”ስለተባረክ ለአንተ ደስ ብሎኛል” የሚለውን ፈተናውን እስክናልፍ ድረስ አሁን ካለን በላይ በፍጹም አይኖረንም፡፡

እግዚአብሔርን የሆነ ነገር ጠይቃችሁት እስካሁን ካልሰጠሰችሁ እየያዘባችሁ እንዳልሆነ እርግጠኛ ሁኑ፡፡ በቀላሉ ቅናትን አስወግዳችሁ አንደኛ ነገራችሁ እርሱን ማድረጋችሁን እርግጠኛ መሆን ይፈልጋል፡፡

እግዚአብሔር በሁሉም ነገር እንድንበለጽግ ይፈልጋል፡፡መልካምነቱን እና እኛን እንዴት እንደሚንባከበን ሰዎች እንዲያዩለት ይፈልጋል፡፡ነገር ግን በረከቶቹን ከምንፈልገው በላይ እሱን ልንፈልገው ይገባል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ  ለቅናት እና የሰውን ለመመኘት በህይወቴ ክፍተት የፈጠርኩበትን አቅጣጫ አሳየኝና በህይወቴ ቀዳሚ የማደርጋቸውን ነገሮች እንዳስተካክል እርዳኝ፡፡ከበረከቶችህ በላይ አንተን መሻት እፈልጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon