ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና። – ማቴ 18፡20
መጽሐፍ ቅዱስ በማስማመት ዉስጥ ሐይል አለ ይላል፡፡ በተለይም ይህ በጋብቻ እዉነት ነዉ፡፡ እኔና ባለቤቴ ዳዊት ተቃራኒ የሆኑ ስብዕናዎች አሉን፡፡ ሆኖም እግዚአብሔር የበለጠ ባቀራረበን ቁጥር የበለጠ ተመሳሳይ ሀሰብና በየቀኑ የበለጠ የሚመሳሰል ነገር ላይ እየደረስን ነዉ፡፡ አሁንም ሁለት የተለያየ ስብዕና ነዉ ያለን ነገር ግን እግዚአብሔር ልዩነታችንን በዓላማ እንዳመጣዉ ማየት እንችላለንለ፡፡
በጋብቻችሁ እንዲሁም በጸሎት ህይወታችሁ ሀይል ከፈለጋችሁ በጋራ መሄድ አለባችሁ፡፡ ትልቁ ጥያቄ እንዴት ነዉ የማይስማሙ ጥንዶች መስማማት የሚማሩት? የሚል ነዉ፡፡ ስምምነት የሚመጣዉ ሰዎች ራስ ወዳድ መሆን ሲያቆሙ ነዉ፡፡ ራስ ወዳድነት በሳል ያልሆነ ለራስ ማሰብ ነዉ፡፡ ቁልፉ ነገር ሌላ ሰዉ ምን ይፈልጋል ብሎ ማሰብ ነዉ ፤ ራስህን ትሁት ለማድረግ ፈቃደኛ ሁን፤ አንተ ማድረግ የምትችለዉን አድርግ፡፡
ይህ ሲሆን በጌታ ፊት በስምምነት መኖር ትችላላችሁ ፤ ደግሞም ሁለት ወይም ሦስት ቢሰበሰቡ ፤ እግዚአብሔር እዚያ ከእነርሱ ጋር ነዉ፡፡ ስለዚህ ዛሬ ስምምነትን ለመፈለግና በጌታ ፊት በአንድነት ለመኖር ምረጡ፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ! በጋብቻዬ የስምምነትን ኃይል መለማመድ እፈልጋለሁ፡፡ ያለስስት መኖር እንድንችል እርዳን፡፡