በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን፡፡ – ሮሜ 8፡37
እግዚአብሔር የወደፊት ህይወትችን ሕልምን ይሰጣል ግን እነዚህ ሕልሞች የሚደረስባቸው ላይመስሉ ይችላሉ፡፡ ይሄም ፍርሃትን ሊያሳድርብን ይችላል፡፡ ፈጽሞ በሕልማችሁ ላይ ተስፋ ላለመቁረጥ የተነሳችሁ ከሆነ ዕድሎችን ሁሉ መጠቀምና ብርቱዎች መሆን ይገባችኋል፡፡ ብርታት የፍርሃት አለመኖርን አያሳይም ፤ ብርታት እየፈሩ እንኳን ወደፉት መግፋት ነው፡፡ የሚያስፈሩ እና የሚጋፉ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ የድፍረት እና የብርታት ጸጋ እንዲሰጠን ወደ እግዚአብሔር መጸለይ እና ፍርሃት ቢሰማን እንኳን መንገዳችንን መቀጠል ነው፡፡
የፍርሃት መንፈስ ሁሌም ወደፊት እንዳትሄድ ዘወትር ይተጋል፡፡ ጠላት ለክፍለ ዘመናት ፍርሃትን የጦር መሳሪያው አድርጎ ተጠቅሞበታል ሰዎችን ለማስቆም፡፡ ዛሬም ይህን ስልቱ የሚቀይር አይደለም፡፡ ፍርሃትን ማሸነፍ ይቻላል ምክንያቱም በወደደን በክርስቶስ ከአሸናፊዎች ሁሉ እንበለጣለን፡፡
ቆራጥ በመሆን ፍርሃት ሲመጣባችሁ ፊትለፊት እንድትጋፈጡት አበረታታችኋለሁ፡፡ ጸንታችሁ ቁሙ ፣ በእግዚብሔር ታመኑ እና እርሱም ዘወትር ከእናንተ ጋር እንደሆነ እወቁ፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ ብፈራም አንኳ በቃልህ አምናለሁ ፤ ቃልህ ከአሸናፋች በላይ እንደሆንኩ ይናገራል፡፡ የሰጠኸኝን የትኛውኑም ሕልሜን ስለምትወደኝ እና ድልን ስለሰጠኸኝ እወረሳለሁ፡፡