ከአጥሩ ጥሰህ ዉጣ

ከአጥሩ ጥሰህ ዉጣ

ወዳጅ ሆይ፥ በጎ የሆነውን እንጂ ክፉን አትምሰል። በጎ የሚያደርግ ከእግዚአብሔር ነው፤ ክፉን የሚያደርግ ግን እግዚአብሔርን አላየውም። – 3 ዮሐ 1፡11

አንዳንድ ጊዜ በዓለም ያሉ ሰዎች እነርሱን እንድንመስል ይፈልጋሉ፡፡ መምሰል ማለት “በባህርይ መመሳሰል፣ ብዙዎቹ እንሚያደርጉት ምሳሌአቸዉን መከተል” ማለት ነዉ፡፡

ሮሜ 12፡12 ይህንን ዓለም አትምሰሉ ይለናል፡፡ ደግሞም 3 ዮሐ 1፡11 መልካምን ነገር እንጂ ክፉን አትከተል ይለናል፡፡

ሰዎች ሁል ጊዜም እንድንመስላቸዉ ይፈልጋሉ ያንን የሚያደርጉት በከፊል ለራሳቸዉ ሲሉ ነዉ፡፡ የሚያደርጉትን ሌላ ሰዉ እያደረገ ከሆነ የተሻለ ይሰማቸዋል፡፡ ሌሎች ራሰቸዉን ይሁኑ ብለዉ ራሳቸዉን የሆኑ ጥቂት ሰዎች ናቸዉ፡፡

ሁላችንም እንደዛ ብናደርግ ዓለም እንዴት የተሻለች ልትሆን እንደምትችል አስበህ ታዉቃለህ? እያንዳንዱ ሰዉ ሌሎች ራሳቸዉን ይሁኑ ብሎ ማንነቱን ቢቀበል አንዳችን ሌሎቻችንን ለመምሰል ባለጣርን ነበር፡፡

ዛሬ የዓለምን ሳጥን እንድትሰብርና ክርስቶስን መምሰል እንደምትችል እንድታምን ላበረታታህ እፈልጋለሁ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ! ዓለምን ከመምሰል ዉድቀት ጠብቀኝ ፤ መልካም ነገር እንድከተልና ክርስቶስን እንድመስል እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon