ከእግዚአብሔር ጋር ስለ ራሱ ስለ እግዚአብሔር አውራ

የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ በሰማይ የምትኖር አምላክ አይደለህምን? የምድር ሕዝቦችን መንግሥታት ሁሉ የምትገዛ አይደለህምን? ኀይልና ሥልጣን በእጅህ ነው፤ ሊቋቋምህም የሚችል ማንም የለም። (2 ዜና. 20፡ 6)

ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ችግር በገጠመው ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ሄደ። ነገር ግን እርሱ ወደ እግዚአብሔር ሄዶ ስለ ችግሩ አልነበረም የተናገረው፤ ወደ እግዚአብሔር ሄዶ ስለ እግዚአብሔር ማንነት ነበር የተናገረው። ስለ ችግሮቻችን ከእግዚአብሔር ጋር ከመነጋገር ይልቅ፣ ስለ ራሱ ስለ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር መነጋገር ይኖርብናል። እንዴት ያለ ድንቅ አምላክ እንደሆነ ከእሱ ጋር መነጋገር አለብን፣ ለእኛ እንዴት መልካም እንደሆነ፣ ባለፉት ጊዜያት ምን እንዳደረገ፣ ደግሞም ከታላቅነቱ የተነሳ ምን ሊያደርግ እንደሚችል የምናውቀውን ከእርሱ ጋር መነጋገር አለብን። በዚህ መንገድ እሱን ካወደስነው እና ካመለክነው በኋላ ስለ ችግሩ ማውራት እንችላለን።

ችግሮች ሲያጋጥሟቸው ብቻ የሚጠሩኝን ጥቂት ሰዎች ማስታወስ እችላለሁ፣ ያ ደግሞ ይጎዳኛል ምክንያቱም እነርሱ ለእኔ ፍላጎት እንደሌላቸው ነገር ግን ለእነሱ ማድረግ የምችለውን ነገር ብቻ እንደሚፈልጉ ስለሚሰማኝ ነው ። እርግጠኛ ነኝ እናንተም እንዲህ ዓይነት ነገር እንደግጠማችሁ እና በተመሳሳይ መንገድ እንደተሰማችሁ እርግጠኛ ነኝ። እነዚህ ሰዎች እራሳቸውን ጓደኛዬ ብለው ሊጠሩ ይችላሉ፣ ግን እውነቱ እነሱ ጓደኞቼ አይደሉም። እርግጥ ነው፣ ጓደኞች ለችግር ጊዜያት ናቸው፣ ነገር ግን ለእነዚያ ጊዜያት ብቻ የሚያስፈልጉ አይደሉም። ጓደኞች እንዲሁ ለመልካም ጊዜያትም ናቸው። ከጓደኞቻችን ጋር የምናሳልፈውን ጊዜ ስለ ችግሮቻችን ብቻ እያወራን ማሳለፍ የለብንም፤ እነሱን ማበረታታት፣ አድናቆትን በማሳየት እና በቃላት እና በድርጊት በመደገፍ ጭምር እንጂ።

ዛሬ ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ በምታሳልፍበት ሰዓት፣ ችግሮችህን ከመጥቀስህ በፊት ስለእርሱ እና ለአንተ ስላደረገው መልካም ነገር ሁሉ ከእሱ ጋር እንደምታወራው እርግጠኛ ሁን።


አብርሃም የእግዚአብሔር ወዳጅ ነበር፤ እኔም የእግዚአብሔር ጓደኛ መሆን እፈልጋለሁ፣ እናም አንተም እንዲሁ እንደምትፈልግ አምናለሁ። እግዚአብሔር የእኛ ችግር ፈቺ ብቻ አይደለም። እሱ ሁሉ ነገራችን ነው። ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ ስለራስህ ከማውራትህ በፊት እግዚአብሔርን ስለራሱ አውራው።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon