ከዕዳ ነጻ የሆነ ህይወት መኖር

እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፥ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታልና። – ሮሜ 13:8

ገንዘብ የሚደርስብን ዉጊያ መንፈሳዊ ዉጊያ እንደሆነ መረዳት ጠቃሚ ነዉ፡፡ ጠላት ከአቅማችን በላይ እንድናወጣ ይፈትነንና ጫና ዉስጥ አስገብቶ ከእግዚአብሔር ጋር ካለን ጉዞ ሊያስተጓጉለን ይፈልጋል፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱ ሊሰጠን ያሰበዉን ህይወት፣ የጽድቅ ህይወት፣ በመንፈስ ቅዱስ የሆነ ሰላምና ደስታ ለመኖር ግብ ሊኖረን ያስፈልጋል፡፡ በጫናና በገንዘብ ዕዳ ዉስጥ እየተጨናነቅን ካለን ይህንን ማድረግ አንችልም፡፡

መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነዉን ገንዘብ ማስተዳደሪያ መንገድ በመከተል ከዕዳ ነጻ የሆነ ህይወት መኖር ይቻላል፡፡ ባለቤቴ ዳዊት እንዲህ ይላል፤ እኛ በአቅማችን መኖርን ከተማርን፣ በገቢያችን መጠን፣ እግዚአብሔር ይባርከናል አቅማችንም ይለጠጣል ከዚያም ብዙ እናገኛለን፡፡  ሉቃስ 19፡17 በጥቂቱ ስንታመን እግዚአብሔር እንደሚደሰትብንና በብዙ ነገር ላይ እንደሚሾመን ይናገራል፡፡

ስለዚህ እግዚአብሔር ከሰጠህ በላይ በሆነ ነገር ለመኖር የመሞከር ወጥመድ ዉስጥ አትግባ ፡፡ በገደብህ በመጽናት ከዕዳ ነጻ የሆነ ህይወት ኑር፡፡ ከዚያ እግዚአብሔር እነዚያን እንዲያሰፋ ጠይቀዉ፡፡

የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! በፋይናንሴ ያለዉን መንፈሳዊ ዉጊያ ማሸነፍ እፈልጋለሁ ስለዚህ በእዳ መኖርን አስወግዳለሁ፡፡ ካለኝ በላይ በማጥፋት ፈተና ዉስጥ አልገባም በምትኩ አንተ ለሰጠሀኝ ገደብ ተማኝ እሆናለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon