ሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው። – መክብብ 3፡1
መክብብ 3፡1 የሚነግረን ለሁሉም ጊዜ እንዳለዉ ነዉ፡፡ ሁላችንም በተመሳሳይ ጊዜ በተመሳሳይ ቦታ አንኖርም፡፡ አንተ በመዝራት ወቅት እንዳለህ ነዶ የሚሰበስብ ሰዉ ሊኖር ይችላል፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ጊዜ ልክ እንዳንተ እነርሱም የመዝራት ወቅት እንደነበራቸዉ አስታዉስ፡፡
የዘር ጊዜ የሚወክለዉ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምንማርበትን ወቅት እንደሆነ ነዉ፡፡ እያንዳንዱ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምመርጥበት ጊዜ የዘር ጊዜ ነዉ በሂደት የአጨዳ ጊዜ ወደ ህይወቴ ይዞ ይመጣል፡፡
በዘርና በአጨዳ ጊዜ መካከል ያለዉ ወቅት የመጠበቅ ጊዜ ይባላል፡፡ ሥሮች ወደ ታችኛዉ የመሬት ክፍል ይሰዳሉ፡፡ ይህ እንዲሆን ጊዜና መሬት ያስፈልጋል፡፡ ከመሬቱ በላይ ምንም ነገር እየተከሰተ መሆኑን መናገር አትችልም፡፡
የመታዘዝ ዘር ከዘራን በኋላ፤ ምንም እንደማይፈጠር እናስብ ይሆናል ነገር ግን እኛ ማየት በማንችልበት ዉስጠታችን አንዳች መልካም ነገር እየተከሰተ ነዉ፡፡ ልክ ዘር ከመሬት ሲወጣ የሚያምርና አረንጓዴ ሆኖ እንደሚበቅል ሁሉ በህይወታችን የዘራነዉ የመታዘዝ ዘር በመጨረሻ እግዚአብሔር ለህይወታችን ያቀደዉን ዉብ ፍሬ ይዞ ይበቅላል፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
ጌታ ሆይ፤ ለማጨድ መዝራት ግድ እንደሆነ አዉቃለሁ፤ ምንም እንደማይከሰት ቢሰማኝም በጉጉት እጠብቅሃለሁ፤ በትክክለኛዉ ጊዜ ወደ አጨዳ እንደምታመጣኝ በማወቅ አንተን አምንሃለሁ፡፡