ከዲያብሎስ ራቁ

ከዲያብሎስ ራቁ

በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና። – ያዕቆብ 1፡12

እኔ እንደማምነዉ ፈተናን መረዳትና አጥብቆ መቃዎም ከዲያብሎስ የምንርቅበት ብቸኛዉ መንገድ ነዉ፡፡ ያዕቆብ 1፡12 የሚለዉ በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና ነዉ፡፡ በፈተና መጽናት ማለት በመጥፎ ገጠመኞች ዉስጥ ተስፋ ሳይቆርጡ ማለፍ፤ ዲያብሎስን ማራቅ ማለት ነዉ፡፡

በተጨማሪም መጽናት ማለት በፈተና ዉስጥ ስናልፍ አመለካከታችንና መሰጠታችን እንዲለወጥ አለመተዉ ማለትም ነዉ፡፡ ኢየሱስ ሲፈተን ሰዎችን ፈጽሞ በተለየ መንገድ አልያዘም፤ እኛ በመንፈሳዊነት ስንበስል የእርሱን ምሳሌ መከተል እንችላለን፡፡

ኢየሱስ እኛ በፈተና ጊዜ የሚሰማንን ይረዳናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ በህይወታችን ላሉ ድክመቶቻችን ትኩረት እንድንሰጥና መቋቋም እንድንችል ሊረዳን ፈተና እንድንጋፈጥ ይፈቅዳል፡፡ እርሱ እንዲኖርህ የሚፈልገዉ ሁሉ የሚኖርህ ብቸኛዉ መንገድ እርሱ ወደ ፈጠረህ ማንነትህ መምጣት ስትችል ነዉ፡፡ ደግሞም ይህ ብስለት የሚመጣዉ በፈተና ነዉ፡፡

ስለዚህ ታገሽ ለመሆንና በፈተና ጊዜ በእግዚአብሔር ጸጋ በጽናት ለመቆም ወስን፡፡ እሱ ከዲያቢሎስ አንድ እርምጃ ያርቀሃል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ በፈተና ጊዜ አንተ ከእኔ ጋር እንዳለህ አምናለሁ፤ ስለዚህ ዘወትር ከዲያቢሎስ አንድ እርምጃ በመራቅ መታገስና በጽናት መቆም እችላለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon