
ወይስ መጽሐፍ። በእኛ ዘንድ ያሳደረው መንፈስ በቅንዓት ይመኛል ያለው በከንቱ እንደ ተናገረ ይመስላችኋልን? – ያዕ 4:5
ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ትፈልጋለህ? እርሱ ለእኛ የቅርብ መሆን ይፈልጋል፡፡ከላይ ያለዉ ክፍል የሚናገረዉ በእኛ ዉስጥ ያስቀመጠዉ መንፈስ በቅናት ይመኛል እንኳን ደህና መጣህ ብለን እንደንቀበለው፡፡
ስለዚህ ምን ያክል ቅርብ መሆን ትችላለህ? ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ግንኙነት ዘወትር ቅርብ መሆን እንችላለን፡፡ ለነገሩ ከእርሱ ጋር ያለን ቅርርብ ምን ያህል መሆን እንዳለበት የምንወስነዉ እኛዉ ነን፡፡ መንፈስ ቅዱስ በዉስጣችን ቢኖርም ግንኙነት እንድናደርግ አያስገድደንም፤ እኛ እንርሱን ወደ ህይወታችን እንኳን ደህና መጣህ ብለን እንድንቀበለዉ ይፈልጋል፡፡
እግዚአብሔር የፈጠረን ለህብረት ነዉ ከእርሱም ጋር ግንኙነት እንዲኖረን ይፈልጋል፡፡ እርሱ ሊያወራን፣ ሊያደምጠን፣ ሊያስተምረን፣ ሊመራን በአጭሩ የህይወታችን ክፍል ሊሆን ይፈልጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ እኛ የተመረጥን ነን ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ስናደርግ እንታደሳለን፡፡ ከአባት ጋር ጊዜ የማሳለፍ ጥቅም ወሰን አልባ ነዉ፡፡
ጓደኛዬ ከአባት ጋር ህብረት ለመፍጠር እንዳትታክት አበረታታሃለሁ፡፡ እርሱ እየጠበቀህ ነዉ፤ ወደ እኔ ና እያለህ ነዉ፤ ስለዚህ ሂድ በመጋዘኑ ምን እንደተቀመጠልህ ተመልከት፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ከእኔ ጋር ህብረት መፈለግህ አስደንቆኛል፡ እኔም ወደ አንተ መቅረብ እፈልጋለሁ፤ ስለወደድከኝና እኔ ወደ አንተ እንደምቀርብ አንተም ወደ እኔ ስለምትቀርብ አመሰግንሃለሁ፡፡