ዋናው ነገር ለእግዚብሔር መኖር ነው

ዋናው ነገር ለእግዚብሔር መኖር ነው

ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ሰዎች ጋር ራሳችንን ልንመድብ ወይም ልናነጻጽር አንደፍርም፤ እነርሱ ራሳቸውን በራሳቸው ሲመ ዝኑና ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር ሲያነጻ ጽሩ አስተዋዮች አይደሉም። – 2 ቆሮንቶስ 10፡12

ከመንጋው ወጣ ብሎ እግዚአብሔርን መከተል ድፍረት ይጠይቃል፡፡ ሌሎች ምን ይላሉ ብሎ መብሰልሰል ራስን ይጎዳል፡፡ ምንም እንኳን ሰዎች ስለኛ በመልካም ቢያስቡ ደስ ቢለንም በሁሉም ሰው መወደድ ግን የሚቻል አይደለም፡፡

በእግዚአብሔር መንግስት እሳቤ ውስጥ መቼም ቢሆን አለን የምንለውን ነገር መጣል እና ራሳችን ከማንም ጋር በሰዎች መስፈርት ሳናወዳድር ለእግዚአብሔር በመኖር በሕይወት የሚያስፈልገንን ልናገኝ እንችላለን፡፡

መልካም ወዳጆችህ እግዚአብሔር እንድትሆን የፈለገውን ሊረዱህ ይችላሉ፡፡ የእግዚአብሔርን ጥሪ በመከተልህ በክፉ አይፈርጁህም፡፡ በሕይወትህ እርሱን ቀዳሚ እንድታደርግ ያበረታቱሃል፡፡ ሰዎች ካንተ ቢሸሹ እንኳን እርሱ ፈጽሞ ላይተውህ ከቶም ላይርቅህ ቃል ገብቶልሃል፡፡

እግዚአብሔርንና ሰዎችን እኩል ለማስደሰት መሞከር ሕይወትን በግራ መጋባት ከመሙላቱም በላይ የተወሳሰበ ያደረጋል፡፡ ራስን ከማንም ጋር ማነጻጸር የለብህም፡፡ ሰዎች ስለኔ ምን ይላሉ በሚልም መጨነቅ ተገቢ አይደለም፡፡ ለሰራህ ነጻ በመሆን ለእግዚአብሔር ኑር፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

ጌታ ሆይ ዛሬ ላንተ ብቻ ለመኖር እወስናለሁ፡፡ በሰዎች መስፈረት እና መጠባበቅ መኖር እኔን የትም አያደርስም፡፡ ለኔ የምታስፈልገኝ ዋናው ነገር አንተ ነህ፡፡ እንድሆንልህ የምትፈልገውን ሰው መሆን እፈልጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon