…. ውያን ከአንተ በኋላ ናቸውን?

.... ውያን ከአንተ በኋላ ናቸውን?

«… እንዲህም ሆነ፤ ከዚህ በኋላ የሞዓብና የአሞን ልጆች ከእነርሱም ጋር ምዑናውያን ኢዮሣፍጥን ሊወጉ መጡ» (2ኛ ዜና 20፡1)።

በዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሞአባውያን፣ አሞናውያንና ምዑናውያን ከይሁዳ ህዝብና ከንጉሱ ከኢዮሳፍጥ ጋር ለመዋጋት ተሰብስበው ነበር። በሌሎች የብሉይ ኪዳን ክፍሎች ኢያቡሳውያንፀ ኬጢያውያንና ከነዓናውያን በእግዚአብሔር ህዝብ ላይ ችግር ወይም መከራ ፈጣሪዎች ነበሩ። ነገር ግን ዛሬ ደግሞ «ፍርሀት – ውያን»፣ «የገንዘብ እጥረት – ውያን»፣ «የዋስትና ማጣት – ውያን»፣ « የአስቸጋሪ ጉረቤት – ውያን» እና ወዘተ… ከእኛ በኋላ ሊወጉን የሚመጡ ሊሆኑ ይችላሉ።

የሚገርምህ በአሁኑ ሰዓት የትኛውም … ውያን እያሳደዱ ነው? ምንም ይሁኑ ምን ከንጉስ ኢዮሳፍጥ ሊወጉን ለመጡት – ውያን የምንሰጠውን ምላሽ ልንማር እንችላለን። ንጉሱ ለመጣበት ችግር በመጀመሪያ ያደረገው ፍርሃት ነበር። ነገር ግን ከዚያም በፍጥነት ሌላ ነገር አደረገ። ጌታን ለመፈለግ ራሱን አዘጋጀ። በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ እንኳን ቢሆን በመላው ግዛቱ ውስጥ ባሉት ላይ ንጉሱ ጾምን አወጀ። ከጌታም ለመስማት ወሰነ። ከእግዚአብሔር መስማት እንደሚያስፈልገው ያውቅ ነበር። የውጊያ ዕቅድ ማውጣት የሚያስፈልግ ቢሆንም በውጊያው ከእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ ስኬት ሊሰጥ እንደሚችል ያውቅ ነበር።

ችግር በሚያጋጥመን ጊዜ ወደ ሰዎች ለመሮጥ ይልቅ እንደኢዮሳፍጥ ወደ እግዚአብሔር የመሮጥ ልማድ በውስጣችን ማዳበር ይገባናል። በራሳችን ጥበብ ከመደገፍና የሌሎችን አስተያየት ከመፈለግ ይልቅ እርሱን መፈለግ ይጠበቅብናል። ራሳችንን መጠየቅ ያለብን ነገር ቢኖር ችግር በሚያጋጥመን ጊዜ ወደ ስልክ ነው ወይስ ወደ ዙፋኑ ነው የምንሮጠው? እግዚአብሔር ሰዎችን በመጠቀም የምክር ቃላትን ሊናገረን ይችላል፤ ነገር ግን ሁልጊዜ በመጀመሪያ የእርሱን ፊት መፈለግ ያስፈልገናል።

የእግዚአብሔር ድምጽ መስማት ፍርሃትን ለመዋጋት ትልቁ መንገዳችን ነው። ከእርሱ ድምጽን ስንሰማ እምነት ልባችንን ይሞላዋል። ፍርሃትም ከእኛ ለቅቆ ይሄዳል። ከዘመናት በፊት ኢዮሳፍጥ ከእግዚአብሔር መስማት እንደሚያስፈልግ ያውቅ ነበርና እናም በተመሳሳይ ከእርሱ መስማት ይጠበቅብናል። ዛሬ እግዚአብሔርን ለመፈለግና ከእነርሱም ድምጹን ለመስማት እርግጠኛ መሆን አለብን።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ እግዚአብሔር በህይወትህ ካሉ … ውያን ይጠብቅህ ዘንድ ወደ እርሱ ጸልይ

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon