ዐመድህን ስጠው

ዐመድህን ስጠው

ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፣ መተላለፋችንን በዚያው መጠን ከእኛ አስወገደ። – መዝሙር 103፡12

ታምነንበት የተበላሹብንን ነገሮች ለአባታችን ስንተውለት የተበላሻውን ወደ ታምራት ፤ ስህተታችንን ለጥቅማችን የሚቀይርበት ችሎታ አለው፡፡

ኢሳያስ 61፡3 በዐመድ ፈንታ፣ የውበት አክሊል እንድደፋላቸው ቢልም በርካታ ሰዎች ዐመዳችውን ፣ ያለፈ ሕይወታቸውን ዝቃጭ ፣ የውድቀታቸውንና ያለመከናወን ታሪክ መያዝ ይፈልጋሉ፡፡
በእጃችሁ ያለው ዐመድ ጥላችሁ አንዳች አዲስ ነገር ለመያዝ እንድትዘረጉ አበረታታችኋለሁ፡፡ በርካቶች ሌላ እድል እንደሌላቸው ቆጥረው በድሮ ውስጥ ይኖራሉ፡፡ ሁለተኛ እድል ትፈልጋላችሁ? እግዚአብሔር ሁለተኛ ፣ ሶስተኛ ፣ አራተኛ ወይም አምስተኛ ፣ በቃ የሚያስፈልጋችሁን ዕድል እንዲሰጣችሁ ጠይቁት፡፡ እግዚአብሔር በምህረቱ እና በትዕግስቱ ባለጠጋ ነው፡፡ ፍቅራዊ ደግነቱ አይታክትም ፍጻሜም የለውም፡፡ መጽሀፍ ቅዱስ መተላለፍሽን ከአንቺ አስወግጃለሁ ይላል ይህን ካደረገ ደግሞ ራሳችሁን በመተላለፍ ውሰጥ ማስቀመጥ የለባችሁም፡፡

ፈቃደኞች ከሆናችሁ እና ካመናችሁበት ኢየሱስ ከባዱን ቀንበር ሊያነሳ መጥቷል፡፡ እርሱ ከስህተታችሁ ይበልጣል፡፡ ዐመዳችሁን ዛሬ ስጡት፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአበሔር ሆይ አዲስ እድል ልትሰጠኝ ቀርበኸኝ ሳለህ በቀድሞ ሕይወቴ ውስጥ ታስሬ መቀመጤ ለኔ አይበጀኝም ስለዚህም ዐመዴን ሁሉ እበትናለሁ፡፡ የውድቀት ዐመዴን ሁሉ ላንተ እሰጥሃለሁ ፤ የምታጎናጽፈኝንም ውበት ለማየት እጓጓለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon