ዓለም ሳይሆን ምንጫችን እግዚያብሔር ነው

ዓለም ሳይሆን ምንጫችን እግዚያብሔር ነው

ለዘሪ ዘርን፣ ለመብላት እንጀራን የሚሰጥ እርሱ የምትዘሩትን አትረፍርፎ ይሰጣችኋል፤ የጽድቃችሁንም ፍሬ ያበዛላችኋል። – 2 ኛቆሮ 9፡10

የእግዚያብሔር የፋይናንስ ስርዓት ልክ እንደዓለም የገንዘብ ስርዓት አይደለም፡፡ ምንም ነገር በዙሪያችን ቢከሰትም ምንም ስለማንሆን ልንፈራ አይገባም ምክንያቱም እግዚያብሔር ይወደናልንና፡፡

የዓለም የገንዘብ ስርዓት የተረጋጋ አይደለም ፤ የእግዚያብሔር ፍቅር ግን የሕይወታችን መሰረትና የማይለወጥ ነው፡፡ ስለዚህም እግዚብሔር በሚያስፈልገን ጊዜ የየዕለቱን ፍላጎቶቻችንን እንኳ እስከማሟላት ሊረዳን እንደሚችል ልንተማመንበት ይገባል፡፡ ሁለተኛ ቆሮንቶስ 9፡10 የሚያተኩረው እግዚያብሔር የምንፈልገውን እንደሚያደርግልንና የምንበላውን እንደሚሰጠን ነው፡፡

ፈላጎቶቻችንን የሚያቀርብለን እግዚያብሔር ብቻ ነው፡፡ የምንሰራው ስራ ሳይሆን ምንጫችን እራሱ እግዚያብሔር ነው፡፡ ስራ እና የገንዘብ ድጋፎች ሲቋረጡ እግዚያብሔር ግን በማይለወጥና በማይቆጠብ ድጋፉ ከእኛ ጋር ስለሆነ ደጋፊ እንደሌለን ልንሆን አይገባም፡፡በማናስባቸው መንገዶች በመምጣት ይረዳናል፡፡

ማቲ 6፡26 እግዚያብሔር የሰማይ አዕዋፋትን ከተንከባከበ እኛንማ አብልጦ እንደሚለግሰን ማመን ይኖርብናል፡፡ እግዚያብሔር እንደሚያስብላችሁ ታምናላችሁ?


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ ምንም ነገር ቢፈጠር ታማኝ፣ አስተማማኝ ምንጭና የምፈልገውን ሁሉ የምትሰጠኝ አምላክ ስለሆንክ አመሰግንሃለሁ፡፡ ፍላጎቶቼንም ለማሳካት አንተንና አንተን ብቻ እደገፋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon